በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ኔቶ ከሩሲያ ጋር በዩክሬን ጉዳይ ሊሰበሰብ ነው


ፎቶ ፋይል፦ የኔቶ አርማ
ፎቶ ፋይል፦ የኔቶ አርማ

የኔቶ ዋና ፀሃፊ ጄንስ ስቶልተንበርግ በሚቀጥለው ሳምንት ውስጥ ሩሲያ በዩክሬን ድንበር አቅራቢያ ባከማቸችው ሠራዊት ሳቢያ የተፈጠረው ውጥረት በሚረግብበት ሁኔታ ለመምከር፣ በምዕራባውያን አገር ዲፕሎማቶችና ሩሲያ ባለሥልጣናት መካከል የውይይት መድረክ ማዘጋጀታቸው ተገለጸ፡፡

የኔቶና ሩሲያ ስብሰባም፣ የሩሲያና ዩናይትድ ስቴትስ ስብሰባ ከተካሄደ ሁለት ቀን በኋላ፣ በሚቀጥለው ሳምንት ረቡዕ ጥር 4/2014፣ ብራስልስ ውስጥ የሚካሄድ መሆኑን ተነግሯል፡፡

ምዕራባውያን አገሮች፣ ወደ 100ሺህ የሚቆጠር ሠራዊቷን ወደዩክሬን ድንበር ያስጠጋችው ሩሲያ፣ የቀደሞዋን የሶቭየት ኅብረት ግዛት ዩክሬንን ልትወር ትችላለች በሚል መስጋታቸው ተመልክቷል፡፡

ሩሲያ በበኩላ፣ የምዕራባውያን አገሮች ጦር ስብስብ በሆነው ኔቶ፣ አባል ለመሆን የጠየቅችው ዩክሬን፣ የኔቶ አባል እንዳትሆን የማረጋጋጫ ዋስትና እንዲሰጣት ጠይቃለች፡፡ ይህ ከሆነ ብቻ ጦሯን ወደኋላ የምትስብ መሆኑን አስታውቃለች፡፡

ዩናይትድ ስቴትስና ካናዳን ጨምሮ 28 የአውሮፓ አገሮች በድምሩ 30 አገሮች አባል የሆኑበት ኔቶ፣ የአባል አገሮቹ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ከሩሲያ ጋር ስለሚያደርጉት ስብሰባ ለመምከር ከነገ በስቲያ አርብ፣ የቪዲዮ ኮንፈረንስ ማዘጋጀቱን አስታውቋል፡፡

ዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ባይደን፣ ሩሲያ ዩክሬንን የምትወር ቢሆን ወታደራዊ አጸፋ መስጠቱን የማይደግፉ መሆኑን ገልጸው፣ አሜሪካና አጋር አገሮች ጠንካራ የምጣኔ ሀብት ማዕቀብ የሚጥሉ መሆኑን አስታውቀዋል፡፡

XS
SM
MD
LG