በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የዓለም መሪዎች የኮቪድ-19 ወረርሽኝን ለመዋጋት ከሦስት ቢሊዮን ዶላር በላይ ለመመደብ ቃል ገቡ


የኮቪድ-19 ክትባት
የኮቪድ-19 ክትባት

ቤሊዝ ጀርመን ኢንዶኔዥያ ትናንት በጋራ በርቀት የቪዲዮ ጉባዔ ባስተናገዱት በዚህ በዩናይትድ ስቴትስ የተመራ ስብሰባ ላይ የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን ባስተላለፉት መልዕክት ዛሬ ሀገራችን በወረርሽኙ አሳዛኝ ምእራፍ ላይ ነች።

በበሽታው ሳቢያ የሞቱት ሰዎች ቁጥር አንድ ሚሊዮን ሞልቷል ብለዋል፡፡ ባይደን ወረርሺኙን ለመዋጋት የጠየቁት የብዙ ቢሊዮን ዶላር አስቸኳይ ወጪ በዩናይትድ ስቴትስ ኮንግረስ አልተፈቀደላቸውም፡፡

በዓለም ዙሪያም ብዙ ሚሊዮኖች ሞተዋል፡ ህጻናት ያለወላጅ ቀርተዋል። አሁንም በየቀኑ በሺዎች የተቆጠሩ እየሞቱ ነው ያሉት የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት በተቻለን መጠን ተጨማሪ ሰዎች እንዳይሞቱ በመከላከል ያጣናቸውን ሰዎች ማከበር አለብን ብለዋል፡፡

የጣሊያን የጃፓን የኒውዚላንድ የሩዋንዳን ጨምሮ የሀገሮች ተወካዮች እንዲሁም የማይክሮሶፍት መስራቹን ቢል ጌትስን የመሳሰሉ የበጎ አድራጎት መሪዎች በዓለም አቀፉ ጉባዔ ላይ የተካፈሉ ሲሆን በብዙ ቢሊዮን ዶላር የተቆጠረ እርዳታ ለማድረግ ቃል ገብተዋል፡፡

ድጋፉ በክትባት በቴክኖሎጂያዊ እርዳታ አና በመሳሰለው መልክ የሚሰጥ መሆኑ ተመልክቷል፡፡

XS
SM
MD
LG