የታቀደው ሀገራዊ ምክክር “ከህወሓት ጋር ለመደራደር ታስቦ የተዘጋጀ አይደለም” ሲል የኢትዮጵያ መንግሥት አስታውቋል።
ሁሉን አካታች ሀገራዊ ውይይት የማድረግ ሃሣብ ከረዥም ጊዜ በፊት የታቀደ መሆኑን የመንግሥት ኮምዩኒኬሽንስ አገልግሎት ሚኒስትር ደ’ኤታ ከበደ ዴሲሳ ለጋዜጠኞች ገልፀዋል።
በሌላ በኩል ለተባበሩት መንግሥታት ድርጅት እንደፃፉት በተነገረ ደብዳቤ “ህወሓት ለሰላም ሲል ኃይሎቹን ከአማራና ከአፋር ክልሎች እንዲወጡ አዝዟል” ያሉት መሪው ዶ/ር ደብረፅዮን ገብረሚካኤል “በኢትዮጵያ ሁሉን አካታች ሀገራዊ ውይይት እንደሚያስፈልግ” አሳስበዋል።
ጉዳይ ሚኒስትር ደ’ኤታ ሬድዋን ሁሴን ከቱርኩ አናዶሉ የዜና ወኪል ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ ደግሞ “ህወሓት ነፍጥ ካወረደና የሚፈለጉ ወንጀለኞችን አሳልፎ ከሰጠ” በውይይቱ ሊሳተፍ የመቻሉ ዕድል ክፍት መሆኑን ተናግረዋል።
ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።