በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ባንኮች የድንበር አካባቢ ቅርንጫፎቻቸውን ደረጃ ዝቅ እንዲያደርጉ ታዝዘዋል


ባንኮች የድንበር አካባቢ ቅርንጫፎቻቸውን ደረጃ ዝቅ እንዲያደርጉ ታዝዘዋል
please wait

No media source currently available

0:00 0:07:17 0:00

ባንኮች የድንበር አካባቢ ቅርንጫፎቻቸውን ደረጃ ዝቅ እንዲያደርጉ ታዝዘዋል

በአንዳንድ የድንበር አካባቢ ከተሞች ውስጥ የሚገኙ የንግድ ባንኮች ቅርንጫፎች ወደ ንዑስ ቅርንጫፍ ዝቅ እንዲሉ መመሪያ የተላለፈው ከጥቁር ገበያ ጋር የተያያዙ ሕገወጥ እንቅስቃሴዎችን ለመግታት እንደሆነ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገዥ ለቪኦኤ ገልፀዋል።

የሶማሌ ክልሏን የድንበር ከተማ ቶጎ ውጫሌን በመሳሰሉ አካባቢዎች ከ80 ብር በላይ ወጥቶ የነበረው የአንድ ዶላር የጥቁር ገበያ መሸጫ ዋጋ ከአዲሱ መመሪያ ወዲህ እየቀነሰ መምጣቱን የብሄራዊ ባንኩ ገዥ ዶ/ር ይናገር ደሴ ተናግረዋል።

የውጭ ምንዛሪን በጥቁር ገበያ ዋጋ የሚሸጡ የግል ባንኮች ሰለመኖራቸው የሚጠቁሙ መረጃዎችን በተመለከተም እየተጣራ መሆኑን ገዥው አመልክተዋል።

ኢትዮጵያ በጥቂት ዓመታት ውስጥ ገበያ መር ወደሆነ የውጭ ምንዛሪ አስተዳደር ልትገባ እንደምትችልም ጠቁመዋል ዶ/ር ይናገር ጠቁመዋል።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገዥ ዶ/ር ይናገር ደሴን ያነጋገራቸው እስክንድር ፍሬው ነው።

XS
SM
MD
LG