በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በናሚቢያ የምርጫ ጣቢያዎች በድጋሚ ተከፍተዋል


የናሚቢያ የምርጫ ኮሚሽን ባለስልጣን በዊንድሆክ በሚገኘው የናሚቢያ የሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርስቲ ምርጫ ጣቢያ የድምጽ ቆጠራ።
የናሚቢያ የምርጫ ኮሚሽን ባለስልጣን በዊንድሆክ በሚገኘው የናሚቢያ የሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርስቲ ምርጫ ጣቢያ የድምጽ ቆጠራ።

በምርጫ ቁሳቁስ እጥረት ምክንያት ለሁለተኛ ጊዜ የምርጫ ሂደቱን ባራዘመችው ናሚቢያ፣ ዛሬ 36 የምርጫ ጣቢያዎች በድጋሚ ተከፍተው ምርጫ ተካሂዷል።

ረቡዕ እለት የተጀመረው የምርጫ ሂደት ባለፉት ሁለት ቀናት በገጠሙ የቴክኒክ ችግሮች ምክንያት፣ የተረጋጋች እና ሰላማዊ ሀገር በመሆን በምትታወቀው ደቡባዊቷ የአፍሪካ አገር ውጥረት ፈጥሯል። ተቃዋሚዎችም የምርጫውን መዘግየት “አሳፋሪ” ብለውታል፡፡

አንዳንድ መራጮች ፕሬዘዳንታቸውንና፣ ህግ አውጭ አባላትን ለመምረጥ እስከ 12 ሰዓት በምርጫ መስጫ ጣቢያዎች ሰልፍ ላይ ማሳለፋቸው ተገልጿል፡፡ ይህም ናሚቢያ ከደቡብ አፍሪካ ነፃ ከወጣች እ.ኤ.አ. በ1990 ወዲህ፣ በስልጣን ላይ ላለው የደቡብ ምዕራብ አፍሪካ ህዝቦች ድርጅት (ስዋፖ) ፓርቲ የገጠመው በጣም ከባድ ክስ እንደሆነ ተገልጿል።

መራጮን መመዝገቢያ ታብሌቶች በትክክል አለመስራትና የምርጫ ወረቀቶች እጥረት ምርጫው በተጀምረ እለት የገጠሙ ቴክኒካዊ ችግሮች እንደነበሩ ተገልጿል፡፡ ይህን ተከትሎ በመራጮችና ፓርቲዎች ነቀፋ የደረሰበት የሃገሪቱ ምርጫ ኮምሽንም፣ ምርጫውን ለሁለተኛ ጊዜ በማራዘም እስከነገ ቅዳሜ ምሽት ድረስ እንዲካሄድ እንዲወስን አስገድዶታል፡፡

ሁኔታው የተቃዋሚ ፓርቲዎችን ቁጣ ያስነሳ ሲሆን አንዳንዶች የምርጫው ሂደት እንዲቆም ጠይቀዋል። ተቃዋሚ ፓርቲዎች ዛሬ ተገናኝተው የጋራ መግለጫ ለመስጠት ቀጠሮ ይዘው እንደነበረም ገለልተኛ አርበኞች ለለውጥ (IPC) ፓርቲ ተወካይ ክሪስቲን አኦቻመስ ተናግረዋል፡፡

የወጣቶች ሥራ አጥነት እና ከነጻነት በኋላ የተወለዱ አዲስ ትውልድ መፈጠር እ.አ.አ ከ1990 ዓ.ም ጀምሮ ሲገዛ ለነበረው ስዋፖ ፓርቲ የነበረውን ድጋፍ ፈታኝ አድርጎበታል፡፡ በናሚቢያ ከተመዘገቡት መራጮች መካከል 42 በመቶ ያህሉ ከ35 ዓመት በታች ዕድሜ እንደሆኑም የምርጫ ባለስልጣን ገልጸዋል፡፡

ናሚቢያ ዋና የዩራኒየም እና የአልማዝ ላኪ ሀገር ብትሆንም ከሦስት ሚሊዮን በላይ የሚሆነው ህዝቧ በመሠረተ ልማት እና የስራ እድሎች ተጠቃሚ እንዳልሆነ ተንታኞች ይናገራሉ።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG