በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ናሚቢያ የመጀመሪያዋን ሴት ፕሬዝደነት መረጠች


በምክትል ፕሬዝደንትነት ሲያገለግሉ የነበሩት  የስዋፖ ፓርቲው የ72 ዓመቷ ኔቱምቦ ናንዲ የናሚቢያ የመጀመሪያዋ ሴት ፕሬዝደነት
በምክትል ፕሬዝደንትነት ሲያገለግሉ የነበሩት  የስዋፖ ፓርቲው የ72 ዓመቷ ኔቱምቦ ናንዲ የናሚቢያ የመጀመሪያዋ ሴት ፕሬዝደነት

በናሚቢያ አወዛጋቢ በነበረውና ባለፈው ሳምንት በተከናወነው ምርጫ ገዢው ስዋፖ ፓርቲ አሸናፊ እንደኾነ በመታወጁ ደቡብ አፍሪካዊቷ ሀገር የመጀመሪያዋን ሴት ፕሬዝደንት መርጣለች፡፡

በምክትል ፕሬዝደንትነት ሲያገለግሉ የነበሩት የስዋፖ ፓርቲው ኔቱምቦ ናንዲ 57 በመቶ ድምጽ በማግኘት ሲያሸንፉ፣ የዋናው ተቃዋሚ ፓርቲ ዕጩ ደግሞ 25.5 በመቶ በማግኘት ሁለተኛ ኾነዋል።

የተቃዋሚው ፓርቲ የምርጫውን ውጤት እንደማይቀበል አስታውቋል።

የ72 ዓመቷ ኔቱምቦ ናንዲ በማዕድን ሃብቷ በምትታወቀው ደቡብ አፍሪካዊቷ ሀገር ናሚቢያ የተመረጡ የመጀመሪያዋ ሴት ፕሬዝደንት ሲሆኑ፣ ፓርቲያቸው ‘የደቡብ ምዕራብ አፍሪካ ሕዝባዊ ድርጅት’ ወይም በምጻሩ ስዋፖ፣ ናሚቢያ በአፓርታይድ ሥር ከነበረችው ደቡብ አፍሪካ ነፃ ከወጣችበት ከእ.አ.አ 1990 ጀምሮ ሀገሪቱን በማስተዳደር ላይ ይገኛል።

ባለፈው ረቡዕ የተደርገው ምርጫ ለ34 ዓመታት በሥልጣን ላይ የቆየውን ስዋፖ የተፈታተነ ሲሆን ‘ገለልተኛ አርበኞች ለለውጥ’ ወይም አይፒሲ የተሰኘው ተቃዋሚው ፓርቲ የሥራ አጥነትና እኩልነት ያለመኖር ያሰቆጣቸውን ወጣት ድምፅ ሰጪዎች ድጋፍ ያገኘበት ነበር ተብሏል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG