በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በናይሮቢ ቆሻሻ መጣያ ሥፍራ ዘጠኝ አስከሬኖች ተገኙ


ፎቶ ፋይል፦ ቡልዶዘር በሙኩሩ አካባቢ በተፋሰስ መሬት ላይ የሚገኙ ቤቶችን እያፈራረሱ፤ ናይሮቢ ኬንያ እአአ ግንቦት 7/2024
ፎቶ ፋይል፦ ቡልዶዘር በሙኩሩ አካባቢ በተፋሰስ መሬት ላይ የሚገኙ ቤቶችን እያፈራረሱ፤ ናይሮቢ ኬንያ እአአ ግንቦት 7/2024

በናይሮቢ ገቢያቸው ዝቅተኛ የሆኑ ነዋሪዎች በሚኖሩበት የከተማዋ ክፍል በሚገኝ ቆሻሻ መጣያ ሥፍራ ዛሬ ዓርብ ዘጠኝ አስከሬኖች መገኘታቸውን ተከትሎ ነዋሪዎች ቁጣቸውን ገልጸዋል።

በደብብ የመዲናዋ ክፍል አስከሬኖቹ ከተገኙበት አቅራቢያ በሚገኝ ፖሊስ ጣቢያ ቁጣቸውን ለመግለፅ የተሰባሰቡ ነዋሪዎችን ፖሊስ በአስለቃሽ ጭስ በትኗል።

አስከሬኖቹ በፕላስቲክ ከረጢት ተጠቅልለው በቆሻሻው ክምር ሥር እንደተገኙ የዓይን እማኞች ለኤኤፍፒ ዜና ወኪል ተናግረዋል።

“ከፖሊስ ምላሽ እንሻለን። ይህ በአስቸኳይ ምርመራ የሚያስፈልገው ጉዳይ ነው” ስትል የአካባቢው ነዋሪ ሉሲ ናምቢ ተናግራለች፡፡

ሙኩሩ በተሰኘው ሰፈር የታየውን አሳዛኝ ክስተት የከተማዋ ፖሊስ አዛዥ አዳምሰን በንጋይ አረጋግጠዋል።

የሟቾቹን አስከሬን ለመለየትና እና እንዴት እንደተገደሉም ለማወቅ ምርመራ እንደተጀመረ አዛዡ ለጋዜጠኞች ተናግረዋል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG