በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

አርሜንያና አዘርባጃን በተኩስ ማቆም ጥሰት እርስ በርስ ተካሰሱ


ፎቶ ፋይል
ፎቶ ፋይል

የአርሜንያ መከላከያ ሚኒስቴር ዛሬ ንጋት ላይ በዊተር ገጹ ባስተላለፈው መልእክት አዘርባጃን ከባድ መሳያዎች በመተኮስ ዛሬ በናጎርና ካራባኽ የተደረገውን አዲስ የተኩስ ማቆም ስምምነት ጥሳለች ሲል ከሷል።

የአዘርባጃን መከላከያ ሚኒስቴር በበኩሉ ጃብረይል ከተማ አከባቢና በክልሉ ባሉት መንደሮች ላይ ጠላት የከባድ መሳርያ ተኩስ ከፍቷል። የአዘርብጃን ወታደራዊ ሀይልም ተግቢ የምላሽ እርምጃ ወስዷል የሚል መግለጫ አውጥቷል

ሁለቱ ሀገሮች ከዛሬ ጀመሮ ተኩስ ለማቆም አዲስ ስምምነት ማደርጋቸውን ትላንት አስታውቀው ነበር። ለሶስት ሳምንታት ያህል ለሚጠጋ ጊዜ ናጎርና ካርባኽ ላይ ሲካሄድ የቆየውን ተኩስ ለማቆም በሳምንቱ ውስጥ ስምምነት ሲያደርጉ ለሁልተኛ ጊዜ ነው።

አዘርባጃንና አርሜንያ ከዛሬ ጀመሮ የተኩስ ማቆም ስምምነት እንደሚያደርጉ ሁለትም ሃገሮች ትላንት ያስታወቁት የሩስያው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርገይ ላቭሮቭ ከአርሜንያና ከአዘርባጃን አቻዎቻቸው ጋር ከተነጋገሩ በሁዋላ መሆኑ ታውቋል።

XS
SM
MD
LG