በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ናብሮ እሣተ-ገሞራና የምሥራቅ አፍሪካ በረራዎች


የምሥራቅ አፍሪካን አካባቢዎች የሸፈነው የናብሮ እሣተ-ገሞራ ብናኝ፤ የሣተላይት ፎቶ
የምሥራቅ አፍሪካን አካባቢዎች የሸፈነው የናብሮ እሣተ-ገሞራ ብናኝ፤ የሣተላይት ፎቶ

ኤርትራ ውስጥ የፈነዳው እሣተ-ገሞራ ባስነሣው ብናኝ ምክንያት የምሥራቅ አፍሪካ የአየር በረራ መስተጓጎሉ ተገለጠ፡፡

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ባለሥልጣናት እንደገለፁት አየር መንገዱ ወደ ጅቡቲ፣ ሰሜን ኢትዮጵያና ሱዳን ዋና ከተማ ኻርቱም የሚያደርገውን በረራ ማቋረጥ ግድ ሆኖበታል፡፡

ቀደም ሲልም የጀርመኑ ሉፍታንዛ ከአሥመራና ከፍራንክፈርት ወደ አዲስ አበባ የሚያደርገውን በረራ መሠረዙም ታውቋል፡፡

ለአየር መንገድ ኢንዱስትሪ እሣተ ገሞራዎችን የሚከታተለው መሥሪያ ቤት እንዳስታወቀው የነብሮ እሣተ ገሞራ ፍንዳታ ዛሬ፣ ማክሰኞም ቀጥሎ የአካባቢውን አየር በአቧራ ሸፍኖታል፡፡

ፍንዳታው ባለፈው ዕሁድ የኤርትራንና የኢትዮጵያን ወሰን አካባቢዎች በመምታቱ መጠነኛ የመሬት ነውጥ አስከትሎ እንደነበርም ተገልጧል፡፡

ዝርዝሩን ያዳምጡ፡፡

XS
SM
MD
LG