በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የዩናይትድ ስቴትስ አገር ውስጥ ደኅንነት መሥሪያ ቤት ተከሰሰ


ነጭ ላልሆኑ ዜጎች መብት መከበር የቆመው ብሔራዊ ማኅበር /NAACP/ የዩናይትድ ስቴትስ የአገር ውስጥ ደኅንነት መሥሪያ ቤትን ከሰሰ።

ነጭ ላልሆኑ ዜጎች መብት መከበር የቆመው ብሔራዊ ማኅበር /NAACP/ የዩናይትድ ስቴትስ የአገር ውስጥ ደኅንነት መሥሪያ ቤትን ከሰሰ።

ወደ 60ሺህ የሄይቲ ፍልሰተኞች፣ ከመባረር የሚያድናቸውን የዩናይትድ ስቴትስን ጊዜያዊ የመኖሪያ ፈቃድ እንዳያገኙ አግዷል በማለት።

“ሚያሚ ሄራልድ” የተባለው ጋዜጣ ትናንት ረቡዕ እንደዘገበው፣ ክሱን በሜሪላንድ ውስጥ በሚገኘው የዩናይትድ ስቴትስ ወረዳ ፍርድ ቤት የመሰረተው፣ የማኅበሩ ህጋዊ መከላከያና ትምህርታዊ መርጃ መስክ ሲሆን፣ የሄይቲ ፍልሰተኞች ጊዜያዊ የጥበቃ መብት ያለመከበርና በ2019 ከአገር እንዲባረሩ የተላለፈው ውሳኔ ኢ-ፍትሐዊና አግላይም ነው ብሏል።

ክሱ የተመሰረተው በማኅበሩ /NAACP/ እና በሄይቲ ማኅበረሰብ አባላት አማካኝነት መሆኑም ታውቋል።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG