በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ሰሜን ኮሪያ የአጭር ርቀት ሚሳዬል ሙከራዎችን አካሄደች


ሰሜን ኮሪያ የአጭር ርቀት ሚሳዬል ሙከራዎችን አካሄደች
ሰሜን ኮሪያ የአጭር ርቀት ሚሳዬል ሙከራዎችን አካሄደች

የደቡብ ኮሪያ ጦር ኃይሎች ከፍተኛው አዛዥ ካንግ ሁ ፒል፣ ሰሜን ኮሪያ እንዲህ ዓይነቶቹን ጠብ አጫሪ ሙከራዎችን እንድታቆም አገራቸው እያስጠነቀቅች መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ሙከራዎቹ በሁለቱ የኮሪያ ጦሮች መካከል እኤአ መስከረም 19 የተደረገውን ወታደራዊ ስምምነትና የፀጥታው ምክር ቤት ውሳኔዎችን የሚጥሱ መሆኑንም የጦር አዛዡ ገልጸዋል፡፡

ከፍተኛው የጃፓኑ ካቢኔ ሚኒስትር ሂሮካዙ ማትሱኖ ለሪፖተሮች በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ በዛሬው እለት የተካሄደው የሚሳዬል ሙከራና ከደቡብ ኮሪያ ጋር በሚያዋስነው ድንበር አቅራቢያ ባለው የአየር ክልል የተካሄደው የጦር አውሮፕላኖች በረራ፣ ቀደም ባሉ ሙከራዎች የተፈጠረውን ውጥረት የበለጠ ያባባሰው መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ማትሱኖ አያያዘውም ጃፓን ሚሳዬሎችን በአየር ላይ እንዳሉ የማመክን አቅሟን ለማሳደግ የምታደርገውን ጥረት መቀጠል አለባት ብለዋል፡፡

XS
SM
MD
LG