በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ኦን ሳን ሱቺ ፍ/ቤት ቀረቡ


ፎቶ ፋይል
ፎቶ ፋይል

የሚያንማር በጦር ሰራዊቱ ከሥልጣን የተወገደው ሲቪላዊ መንግሥት ርዕሰ ብሄርዋ ኦን ሳን ሱቺ በዛሬው ዕለት ፍርድ ቤት ቀርበዋል።

የጦር ሃይሉ እርሳቸውን እና ሌሎችንም የመንግሥቱ መሪዎች ከሥልጣን አውርዶ አስተዳደሩን ከተቆጣጠረ እና ከአሰራቸው ወዲህ ዛሬ ለመጀመሪያ ጊዜ መታየታቸው ነው።

በበይነ መረብ በቪዲዮ አማካይነት የፍርድ ቤቱ ችሎት ፊት የቀረቡት የሰባ አምስት ዓመቷ ኦን ሳን ሱቺ እንዳየኋቸው ከሆነ በደህና ሁኔታ ላይ ያሉ ይመስላል ብለዋል ጠበቃቸው።

በዛሬው የፍርድ ቤት ችሎት ላይ አቃቤ ህግ በኦን ሳን ሱቺ ላይ ህዝባዊ አመጽ ማነሳሳት እና ያለህጋዊ ፈቃድ በቲሌኮሙኒኬሽን መሳሪያ መጠቀምን የሚከለክለውን ክስ በመጣስ ሁለት አዲስ ክሶች ጨምሮባቸዋል።

ትናንት በሀገሪቱ ዙሪያ በተቃውሞ ሰልፎች ላይ አስራ ስምንት ሰዎች ሲገደሉ ሌሎች ከሰላሳ የሚበልጡ ቆስለዋል፥ ዛሬም የጸጥታ ኃይሎች ያንጎን ከተማ ውስጥ በተቃውሞ ሰልፈኞች ላይ አስለቃሽ ጋዝና በጩኸት ድምጽ ማባረሪያ ፈንጂ ተኩሰውባቸዋል።

XS
SM
MD
LG