በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በሚያንማር በእስር የነበሩ የሮይተርስ ጋዜጠኞች ተፈቱ


በሚያንማር ለሁለት ዓመታት በእሥር ላይ የቆዩት ሁለት የሮይተርስ ዜና አገልግሎት ጋዜጠኞች ዛሬ ተለቀው ቤተሰቦቻቸውን ተቀላቅለዋል።

ጋዜጠኞቹ የተለቀቁት የሃገሪቱ ፕሬዚዳንት ዊን ማይንት ለብዙ ሺህ እሥረኞች ምህረት ካደረጉ በኋላ ነው።

ጋዜጠኞቹ ዋሉን እና ካየ ዋ ሴ በሰባት ዓመት እሥራት እንዲቀጡ ተፈርዶባቸው የነበረው፣ ኦፊሴላዊውን የሚሥጥር ሕግ ጥሳችኋል ተብሎ እንደነበር ይታወሳል።

ሁለቱ ጋዜጠኞች እአአ በ2017 በቁጥጥር ሥር የዋሉት 10 የሮሒንጋ ብሄረሰብ አባላት ኢን ዲን መንደር ውስጥ በፖሊሶችና ወታደሮች መገደላቸውን በመመርመር ላይ እንዳሉ ነበር።

ዛሬ ከእሥር ተለቀው ሲወጡ - ወዳጆችና ቤተሰቦቻቸው በደስታ ተቀብለዋቸዋል።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG