በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ሳን ሱ ኪ ወደ ዋናው ከተማ እስር ቤት ተዛወሩ


ሳን ሱ ኪ
ሳን ሱ ኪ

ከሥልጣናቸው ተወግደው በእስር የሚገኙት የማያንማር መሪ ሳን ሱ ኪ ዛሬ ረቡዕ በአገሪቱ ዋና ከተማ ወደሚገኘው እስር ቤት መዛወራቸው ተነገረ፡፡ የተመሰረተባቸውን ክስ የሚያስችለውም ችሎት ከፍርድ ቤት ወደ እስር ቤት መዛወሩ ተመልክቷል፡፡

ሳን ሱ ኪ በወታደራዊ መንግሥት ተነስተው በቁጥጥር ስር ከዋሉበት እኤአ 2021 መጀመሪያ አንስቶ ቢያንስ ወደ 20 በሚጠጉ ወንጀሎች ተከሰዋል፡፡ ሳንሱኪ ሁሉንም አስተባበዋል፡፡ ምዕራባውያን አገሮች በአስችኳይ እንዲፈቱ የጠየቁ ሲሆን ወታደራዊ መንግሥቱ ጉዳያቸው በገለልተኛ ፍርድ ቤት እየታየ ነው ብሏል፡፡

በሌላም በኩል የማያንማር ወታደራዊ ገዥዎች በሚቀጥለው ዓመት ነጻና ፍትሃዊ ምርጫ ለማድረግ የገቡት ቃል “ለፕሮፖጋንዳ ፍጆታ የዋለ ሀሰተኛ መረጃ ነው፤ ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ በዚህ ፕሮፖጋንዳ መታለል የለበትም” ሲሉ አንድ የተባበሩት መንግሥታት ባለሙያ ተናግረዋል፡፡

በማይንማር የሰብአዊ መብቶች ጉዳዮች ላይ የተካኑት የመንግሥታቱ ድርጅት ባለሙያው ቶን አንድሩ ለአሶሼይትድ ፕሬስ ዛሬ በሰጡት መግለጫ የወታደራዊ መንግሥቱ የምርጫ ወሬ፣ የሳንሱ ኪን መንግሥትን በኃይል ከገለበጠ በኋላ ህጋዊነትን ለማግኘት የሚያደርገው ጥረት አካል ነው ብለዋል፡፡

ባለሙያው አያይዘው “ተቃዋሚዎችህን በሞት ችሎት አስቀምጠህ ነጻና ፍትሃዊ ምርጫ ልታደርግ አትችልም” ማለታቸው ተዘግቧል፡፡

ወታደራዊ መንግሥቱ ሥልጣን ከያዘው ወዲህ እስካሁን ከ2007 በላይ ተቃዋሚዎችን መግደሉ ተመልክቷል፡፡

XS
SM
MD
LG