በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የሚያንማር መሪ ኡን ሳን ሱ ቺ ወደ ራኺኔ ተጓዙ


 ኡን ሳን ሱ ቺ
ኡን ሳን ሱ ቺ

የሚያንማር መሪ ኡን ሳን ሱ ቺ ወደ ታወከው የሃገሪቱ ሰሜናዊ ክፍለ ሃገር ራኺኔ ተጉዘዋል።

የሚያንማር መሪ ኡን ሳን ሱ ቺ ወደ ታወከው የሃገሪቱ ሰሜናዊ ክፍለ ሃገር ራኺኔ ተጉዘዋል።

ሳን ሱ ቺ የሀገራቸው የጦር ሠራዊት በህዳጣኑ የሮሒንግያ ሙስሊሞች ላይ ጭካኔ የተመላበት የጥቃት ዘመቻ ከከፈተ ወዲህ ክፍለ ሀገሩን ሲጎበኙ ይህ የመጀመሪያ ጊዜያቸው ነው።

የማያንማርዋ መሪ ዛሬ “ሞንዳው” በምትባል ከተማ አቅራቢያ የሮሒንግያ ሙስሊም ማኅበረሠብ አባላት ጋር ተገናኝተዋል። ሚያንማርና ባንግላዴሽን ወደሚያዋስነው ድንበር አካባቢም የተጓዙት የሁለቱ ሀገሮች የወዳጅነት ድልድይ ላይ ከድንበር ጥበቃ ፖሊሶች ቤተሰቦች ጋር ቆይታ አድርገዋል።

ኡን ሳን ሱቺ በጉብኝታቸው ባለፈው መስከረም ወር የሮሒንግያ ሙስሊም ታጣቂዎች ከሀገሬው ሚዮ ብሄረሰብ የሆኑ ሥምንት ሰዎችን ጭካኔ በተመላበት መንገድ የገደሉበትን መንደርም መጎብኝታቸው ተገልጿል። የመደርተኞቹ ተወካይ ለቪኦኤ የበርማ አገልግሎት በሰጡት ቃል እንዳሉት አውን ሳን ሱ ቺ በመጎብኘታቸው ሕዝቡ ደስ ብሎታል ነገር ግን ብሶቱን ለመግለፅ በቂ ጊዜ አላገኘም ።

የኖቤል የሰላም ተሸላሚዋ ኡን ሳን ሱ ቺ በቀውሱ አያያዛቸው ምክንያት ከዓለምቀፉ ማኅበረሠብ ብርቱ ነቀፌታ ሲወርድባቸው ሰንብቷል። እሳቸውም ቢሆኑ መጀመሪያ ላይ የሮሒንግያ ላይ ስለሚደርሰው ስቃይ

“መጠነ ሠፊ የተዛባ መረጃ እየተሰራጨ ነው” የሚል አቋም ይዘው አጥብቀው ሲከላከሉ መክረማቸው አይዘነጋም።

የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ባንግላዴሽ ውስጥ ብዙ መቶ ሺህ ስደተኛ የሮሒንግያዎች ወደተጠለሉበት መንደር በዚሁ ሳምንት መጨረሻ መልዕክተኛ እንደሚልክ አስታውቋል።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG