ዋሺንግተን ዲሲ —
ሁለት የሮይተርስ ዜና አውታር ዘጋቢዎች የመንግሥት ምስጢር ይዘዋል ተብሎ የቀረበባቸው የምስክርነት ቃል፣ በፖሊስ የተቀነባበረ በመሆኑ ውድቅ እንዲደረግ የቀረበውን ጥያቄ፣ የማያንማር ዳኛ ውድቅ አደረጉት።
የፖሊስ ሻለቃ ሞ ያን ናይግ በሰጡት ቃል፣ አለቃቸው ጋዜጠኞቹን እንዲከታተሉ ሁለት ፖሊሶች መመደባችን ገልፀው የሰጡት የምስክርነት ቃል፣ ቀደም ሲል በቀረበ ክስ ላይ ከሰጡት ጋር በመቃረኑ ነው በሰዎቹ ላይ ክስ የተመሰረተው።
ተከላካይ ጠበቃ ዩ ኬሂም ማውግ ዛወ ለቪኦኤ በርማ አገልግሎት በሰጡት ቃል፣ የፖሊሱ ሻለቃ የሰጡት የምስክርነት ቃል፣ ሁለቱን ጋዜጠኞች ነፃ ያወጣል ብለው ተስፋ እንደሚያደርጉ ገልጿል።
ዐቃቤ ህግ በበኩሉ፣ የፖሊስ መኮንኑ ቃል ተዓማኒነት እንዳይኖረው ማሳሰቡ ታውቋል።
ሁለቱ የሮይተርስ ዘጋቢዎች በቁጥጥር ሥር የዋሉት ባለፈው ታህሣሥ 12 ቀን መሆኑም ተገልጧል።
የፌስቡክ አስተያየት መስጫ