በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

“ዓለም አቀፍ ማኅበረሰብ ማይናማርን ከጅምላ ሁከት ማዳን አልቻለም” ሪፖርት


በማይናማር ሰሜናዊ ምዕራብ ሳጊንግ ግዛት ውስጥ በዴፓይን ከተማ ጥቃት የደረሰበት ግለሰብ
በማይናማር ሰሜናዊ ምዕራብ ሳጊንግ ግዛት ውስጥ በዴፓይን ከተማ ጥቃት የደረሰበት ግለሰብ

የማይናማር ሠራዊት የጦር ወንጀልና በሰብዓዊነት ላይ የሚፈጸም ወንጀልን በየቀኑ እየፈጸመ እንደሚገኝ አንድ ሪፖርት ይፋ አድርጓል።

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ልዩ ራፖርተር የሆኑት ቶም አንድሩስ ባወጡት ሪፖርት የፆታ ጥቃት፣ ማሰቃየት፣ ሲቪሎችን ሆን ብሎ ዒላማ ማድረግ እና ግድያ በየዕለቱ የሚፈጸሙ መሆናቸውን አመልክተዋል።

ዛሬ ሐሙስ የተለቀቀው ይህ ሪፖርት ዓለም አቀፍ ማኅበረሰቡ በማይናማር ሰዎች ላይ በጦር ተፈጽሟል የተባለውን ይህን የጅምላ ሁከት ማስቆምና መከላከል ባለመቻሉ ነቀፌታ አቅርቧል።

ሪፖርቱ ወታደራዊ ሁንታው በማይናማር ህዝብ ላይ የሚያሳየውን የማያቋርጥ ጭካኔ ፍንትው አድርጉ አሳይቷል ስትል የቪኦኤዋ ሊሳ ሽላይን ከጄኔቭ ዘግባለች።

እንደ ሪፖርቱ ከሆነ ከ28ሺህ በላይ ቤቶችና መንደሮች ሙሉ ለሙሉ በእሳት ጋይተዋል። ህፃናትን ጨምሮ ከ12 ሺህ በላይ የሚሆኑ ሰዎች አሳዛኝ በሆነ ሆኔታ በዘፈቀደ ታስረዋል።

ከአምስት ዓመታት በፊት በሮሂንጂያ ሙስሊሞች ላይ በተፈፀመ ጥቃት 700 መቶ ሺህ የሚሆኑት ነፍሳቸውን ለማዳን ወደ ባንግላዴሽ ሸሽተዋል።

የሪፖርቱ ባለቤት ቶም አንድሩስ እንዳሉት በማይናማር ያሉ በርካታ ሰዎች ዓለም እንደረሳቸው ወይም ዓለም ስለ እነርሱ ግድ እንደማይሰጠው ያምናሉ።

XS
SM
MD
LG