በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የሮሒንግያ ሙስሊሞች ወደ ቀያቸው እንዲመለሱ ስምምነት ተፈረመ

በማያንማር እና ባንግላዴሽ ከጥቃት ሸሽተው ወደባንግላዴሽ የተሰደዱት ብዙ መቶ ሺህ የሮሒንግያ ወደቀያቸው እንዲመለሱ ስምምነት መፈራረማቸውን የሁለቱም ሃገሮች ባለሥልጣናት ገለፁ፡፡

በማያንማር እና ባንግላዴሽ ከጥቃት ሸሽተው ወደባንግላዴሽ የተሰደዱት ብዙ መቶ ሺህ የሮሒንግያ ወደቀያቸው እንዲመለሱ ስምምነት መፈራረማቸውን የሁለቱም ሃገሮች ባለሥልጣናት ገለፁ፡፡

የማያንማር የሠራተኛ ጉዳይ እና የኢሚግሬሽ ሚኒስቴር ቋሚ ተጠሪ ሚዩንት ክያንግ ባንግላዴሽ ሰነዶቹን እንደላከችልን በተቻለ ፍጥነት ልንቀበላቸው ዝግጁ ነን ማለታቸውን ሮይተርስ ዘግቧል።

ወደባንግላዴሽ ተሰደው ካምፖች ውስጥ የሰፈሩት የሮሒንግያዎች ቁጥር ከሥድስት መቶ ሺህ በላይ መሆኑ ይገመታል።

የባንግላዴሽ ማያንማር ስምምነት መፈራረም የተወራው ትናንት የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሬክስ ቲለርሰን ሚያንማር ራኺኔ ክፍለ ግዛት ላይ በሙስሊሞቹ ሮሒንግያዎች ላይ የተፈፀመው ጥቃት የዘር ማጥፋት ተግባር ነው ሲሉ በተናገሩ በማግስቱ መሆኑ ነው።

የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ሁከቱን በዘር ማፅዳትነት ሲገልፀው የትናንቱ የመጀመሪያ ጊዜው ነው።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG