በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

አን ሳን ሱ ቺ ወደቤት ቁም እስረኝነት ተዛወሩ


ፎቶ ፋይል፦ አን ሳን ሱ ቺ
ፎቶ ፋይል፦ አን ሳን ሱ ቺ

የሚያንማር ወታደራዊ መንግሥት በተነሳው የሙቀት ማዕበል ምክንያት በእስር ላይ የሚገኙትን የቀድሞ መሪ አን ሳን ሱ ቺ ከእስር ቤት ወደ ቤት የቁም እስረኝነት መዛወራቸውን አስታወቀ፡፡

አን ሳን ሱ ቺ እና የተወገደው መንግሥታቸው ፕሬዚዳንት የነበሩት ዊን ምይንት በሙቁቱ ማዕበል የተነሳ ከእስር ቤቱ ከተዛወሩ አዛውንቶችና አቅመ ደካሞች መካከል መሆናቸውን ለውጭ መገናኛ ብዙሃን ትናንት ማክሰኞ መግለጫ የሰጡት የወታደራዊ ቃል አቀባይ ተናግረዋል፡፡

ደጋዎቻቸውና የመብት ድርጅቶች ለፖለቲካ ሲባል የተፈበረኩ ናቸው በሚሏቸው በተለያዩ ወንጀሎች 27 ዓመት ተፈርዶባቸው ሳን ሱ ቺ፣ በሚያንማር ዋና ከተማ ኔይፕታው ውስጥ እስር ላይ ናቸው፡፡

ስምንት ዓመት የተፈረደባቸው የቀድሞው ፕሬዚዳንት ዊን ሚይንት የታሰሩት በምያንማር ባጎ ክፍለ ግዛት ታውንጉ ውስጥ ነው፡፡

በሌላ በኩል ወታደራዊው መንግሥት በዚህ ሳምንት በሚያንማር የሚከበረውን አዲስ ዓመት ምክንያት በማድረግ ዛሬ ከ3,000 በላይ ለሚሆኑ እስረኞች ምህረት ሰጥቷል፡፡

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG