ዋሺንግተን ዲሲ —
ሁለት ዓመታት ባልሞላ ጊዜ፣ በዛው ሥፍራ በሮሂንጂያ ሙስሊሞች ላይ አስከፊ ጉዳት አድርሶ ነበር ይላል አምነስቲ።
የክፍለ ግዛቱ የቡድሀ ዕምነት ተከታዮች የውስጥ አስተዳደር መብት እንዲከበር የሚንቀሳቀሱት የአራካን አማፅያን ቡድንን ለመውጋት ወታደራዊው ኃይል በብዙ ሺህ የሚቆጠሩ ወታደሮችን ወደ ራኺን ልኳል።
የሰብአዊ መብት ተሟጋቹ ድርጅት ዛሬ ባወጣው ዘገባ የምያንማር ወታደሮች ፈፀመዋቸዋል ያላቸው የጦር ወንጀሎችን ዘርዝሯል።
ወንጀሎቹ ግድያዎችን፣ በገፍ ማሰርን፣ ሰቆቃ መፈፀምንና እንደወጡ መቅረትን ያካተቱ ናቸው።
በምሥራቅና በደቡብ ምሥራቅ እስያ የአምነስቲ ቀጠናዊ ሥራ አስኪያጅ ኒኮላስ ቤኩሊን ወታደራዊው ኃይል በአሁኑ ወቅት ራኺን ውስጥ በሚወስደው ዕርማጃ ሲቪልችን እያሸበረ ነው ብለዋል። ይሁንና የአርካን አማፅያንም በሲቪሎች ላይ በደል እንደሚፈጽሙ አምነስቲ ሳይገልፁ አላለፈም።
የፌስቡክ አስተያየት መስጫ