በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በአዲስ አበባ የሙስሊሙ ጥያቄ


በአዲስ አበባው አወሊያ ትምህርት ቤት አካባቢ፣ ላለፉት ሰባት ሣምንታት ሕዝባዊ ሰልፍ እንደሚካሄድና ባለፈው ዐርብም ለሰባተኛ ጊዜ የወጣው ሕዝብ ቁጥር መቶ ሃምሣ ሺህ እንደነበር ተሰምቷል።

በአዲስ አበባው አወሊያ ትምህርት ቤት አካባቢ፣ ላለፉት ሰባት ሣምንታት ሕዝባዊ ሰልፍ እንደሚካሄድና ባለፈው ዐርብም ለሰባተኛ ጊዜ የወጣው ሕዝብ ቁጥር መቶ ሃምሣ ሺህ እንደነበር ተሰምቷል።

ይህ ለረዥም ጊዜ ተካሄደ የተባለው ሕዝባዊ ስብስብ ዓላማ ምንድነው? እውን የሕዝቡ ቁጥርስ ትክክል ነው?

የሙስሊም ማኅበረሰብ የሕዝብ ጥያቄ አቅራቢ ተብሎ የተወከለው ኰሚቴ ጊዜያዊ ሰብሳቢ የሆኑት አቶ አቡባከር አሕመድ መሐመድ በወዲያኛው ሣምንትና ባለፈው ሣምንት ጁምዐ የወጣው ሰው ከመቶ ሺህ በላይ እንደሚገመት ለቪኦኤ አረጋግጠዋል፡፡

ሙስሊሙ ኅብረተሰብ ሦስት ጥያቄዎችን ማንሣቱን የጠቆሙት አቶ አቡባከር አሕመድ መሐመድ ሲዘረዝሩ፣ የሙስሊሙን ተቋም የሚመራው ሙስሊሙ ያልወከለው ወይም ያልመረጠው አካል በመሆኑ ያልወከሏቸው መሪዎች ወርደው በተመረጡ እንዲተኩ፤ በሙስሊሙ ማኅበረሰብ ላይ እየተጫነ ነው ያሉት አስተምህሮት እጅን በመጠምዘዝ እየተደረገ ያለ በመሆኑ የሚቃወሙት ስለሆነ እንዲቆም፤ በአወሊያ ተቋም ላይ ቀደም ሲል የተጠቀሰው አካል የተለያዩ ችግሮችን እየፈጠረ በመሆኑ እጁን እንዲያነሣና ተቋሙ በተመረጠ ቦርድ እንዲመራ የሚሉ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡

በሕግ ሊጠየቁ የሚገባቸው ካሉም ኅብረተሰቡ እንዲጠየቁ የሚፈልግ መሆኑንም አቶ አቡባከር አመልክተዋል፡፡

ጥያቄአቸው እስከአሁን መልስ ያላገኘ ቢሆንም መንግሥት የካቲት ሃያ ስድስት መልስ ይሰጠናል ብለው እየጠበቁ መሆኑን ገልፀዋል፡፡

ባለፈው ዐርብ ስብሰባ በአወሊያ ትምህርት ቤት ሕዝባዊ ስብሰባ መካሄዱን ከተረዳን ጀምሮ ቪኦኤ ከኢትዮጵያ እሥልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት መልስ ለማግኘት ጥረት ሲያደርግ ቆይቷል፡፡

በተለይ ሰኞ የካቲት 14 ቀን በስልክ ያገኘናቸው የጠቅላይ ምክር ቤቱ የፀጥታና የሰላም ጉዳዮች አስተባባሪ ሃጂ ጀማል መሃመድ በማግስቱ ማክሰኞ መልስ ሊሰጡን ቃል ገብተው የቪኦኤ የአማርኛ አገልግሎት ዘገባውን ለአየር እስካበቃበት ደቂቃ በተደጋጋሚ ስልክ ቢደወልላቸውም ስልካቸው ሣይነሣ ቀርቷል፡፡

አቶ አቡባከር አሕመድ መሐመድን ያነጋገችውን የትዝታ በላቸውን ቃለ ምልልስ ያዳምጡ፡፡

XS
SM
MD
LG