በፌደራል ዐቃቤ ሕግ በሽብርተኝነት ክስ የተመሰረተባቸው ጋዜጠኛ ካሊድ መሐመድና ዳርሰማ ሶሪን ጨምሮ 19 ተከሳሾች ናቸው። 19ኛ ወንጀል ታኅሣሥ 12 ቀን 2009 ዓ.ም በዋለው ችሎት ለዛሬ ቀጠሮ ሰጥቶ የነበረው ዐቃቤ ሕግ ያቀረበውን ማስረጃ መርምሮ ተከሳሾቹ "ጥፋተኛ” ናቸው ወይም “ጥፋተኛ አይደሉም” የሚል ውሳኔ ለመስጠት ነበር።
በዚህም መሰረት ፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት 19ኛ ወንጀል ችሎት ሁለት ጋዜጠኞችን ጨምሮ በ19 የሙስሊም ማኅበረሰብ ጥያቄዎች መፍትሔ አፈላላጊ ኮሚቴ አባላት በተያያዘ በተከሰሱ ተከሳሾች ላይ የጥፋተኝነት ውሳኔ አስተላለፈ። ፍርድ ቤቱ ተከሳሾቹ የቅጣት አስተያየታቸውን በጽቤቱ በኩል እንዲያስገቡ ትእዛዝ ሰጠቶ ለፍርድ ውሳኔው ለታህሳስ 25 ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጠቷል። ጠበቃቸውን አነጋግረናል።
ጽዮን ግርማ በዛሬ ችሎት ተከሳሾቹን ወክልው ችሎት የቆሙትን ጠበቃ አቶ ሰኢድ አብደላን አነጋግራለች።
ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምጽ ፋይል ያድምጡ።