በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ኢላን ማስክ የትዊተር ቦርድ አባል ሆኑ


ፎቶ ፋይል፦ ዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ የኤሌክትሪክና የጠፈር ተሽከካሪዎች አምራች ባለቤት የሆኑት ባለጸጋው ኢላን መስክ
ፎቶ ፋይል፦ ዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ የኤሌክትሪክና የጠፈር ተሽከካሪዎች አምራች ባለቤት የሆኑት ባለጸጋው ኢላን መስክ

ዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ የኤሌክትሪክና የጠፈር ተሽከካሪዎች አምራች ባለቤት የሆኑት ባለጸጋው ኢላን መስክ የማህበራዊ ሚዲያው ትዊተር ቦርድ አባል መሆናቸው ተገለጸ፡፡

ኢላን ማስክ የቦርድ መሆናቸው የተገለጸው በትዊተር ውስጥ ከ9ከመቶ ብልጫ በመያዝ ትልቁን ሼር ያላቸው መሆኑ በተነገረ ማግስት መሆኑን ተመልክቷል፡፡

ኢላን ማስክ በቦርድ አባልነታቸው ህግ መሰረት ከትዊተር 14.9 ከመቶ በላይ የባለቤትነት ድርሻ ሊይዙ እንደማይችሉ ተነግሯል፡፡

በጎላ የትዊተር ተጠቃሚነታቸው የሚታወቁት ኢላን ማስክ ወደ 80 ሚሊዮን ተከታዮች ያላቸው ሲሆን የዩናናይትድ ስቴትስን ህገመንግሥት በመጥቀስ ለመጀመሪያ ጊዜ ትዊተር ሀሳብን በነጻ የሚደግፍ ተቋም ለማድረግ የጠየቁና መሆናቸው ተነግሯል፡፡

ራሳቸው እዚያው ትዊተር ላይ 2ሚሊዮን ከሚደርሱ ሰዎች ካሰባሰቡት የህዝብ አስተያየት ድምጽ 70 የሚሆኑት ተጠቃሚዎች ትዊተር ሀሳብን በነጻነት ለመግለጽ ያልቆመ መሆኑን መመስከራቸው ተመልክቷል፡፡

የቦርድ አባል መሆናቸው ከተነገረ በኋላ ኢላን ማስክ ባወጡት የትዊት መልዕክልት በቅርብ ወራት ውስጥ በትዊተር ላይ ትልቅ ለውጥ ለማምጣት ከቦርድ አባላቱ ጋር እንደሚሰሩ አስታውቀዋል፡፡

XS
SM
MD
LG