በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ኬንያ ውስጥ ባለ ብዙ ፎቆች ህንጻ ተደምርሶ ሁለት ሰዎች ሞቱ

ከኬንያ ዋና ከተማ ናይሮቢ ወጣ ብሎ በሚገኝ ሩዋካ በተባለው አካባቢ ግንባታ ላይ የነበረ አንድ ባለብዙ ፎቆች ህንጻ ዛሬ ሀሙስ ተደርምሶ ሁለት ሰዎች መግደሉን የአገሪቱ ባለሥልጣናት አስታወቁ።

ህንጻው ከወደቀበት አጠገብ ከነበረው የመኖሪያ ቤት ውስጥ የነበሩ ሦስት ሰዎች በአደጋ ጊዜ ሰራተኞች በህይወት መትረፋቸው ተነገሯል።

ዛሬ ጧት መደርመሱ የተነገረው ህንጻ በሳምንቱ ውስጥ ለሁለተኛ ጊዜ መሆኑን የግንባታ ባላሥልጣናት የገለጹ ሲሆን ይህን መሰሉ ደህንነታቸው ያልተጠበቁ የህንጻዎች ግንባታ በከተማውና ወጣ ባሉ አካባቢዎች እየተለመዱ መምጣታቸውን ሲያስጠነቅቁ እንደነበር ተመልክቷል።

ባለፈው ማክሰኞም በከተማው ውስጥ በተደረመሰው ባለብዙ ፎቆች ህንጻ የኮንስትራክሽን ሰራተኞች መውጫ አጥተው እንደነበር ተገልጧል።

ከቅርብ ጊዜዎቹ አደጋዎች በኋላ የአዳዲስ ህንጻዎችን ግንባታ ደህንነት አስመልክቶ ጥያቄ ያነሱት ዊሊ ካሙ የተባሉ የአካባቢው ነዋሪ እንዲህ ብለዋል፡፡

“በነገራችን ላይ ይህ በኪያምቡ ውስጥ ከፍተኛ ሥጋት ሆኗል። ይህ የመጀመሪያው ህንጻ ወይም ክስተት አይደለም። በዚህ አንድ ሳምንት ውስጥ ብቻ ሁለት ህንፃዎች ፈርሰዋል።

በዚህም የንፁሀን ህይወት አጥተናል። ባለፈው ወር የቀበርናቸው አንዲት ሴት እና ልጆቿ ነበሩን። እነሱም ተመሳሳይ እጣ የደረሳቸው ንጹሃን ናቸው።

እነዚህ እኮ በህንፃው ውስጥ አልነበሩም፣ ግን ከቤታቸው አጠገብ ያለ ህንፃ ፈርሶ እናት እና ልጆቿ እንደዘበት ሞተዋል። ስለዚህ እኛ የምንጠይቀው ይህ የወረዳው መንግሥት ሥራ ነው፣ የብሄራዊ መንግሥቱ ሥራ እንኳን አይደለም። የህንጻዎች ንድፍን ጨምሮ ሁሉንም የግንባታ ፈቃዶች መስጠት የወረዳው መንግሥት ሥራ ነው።”

የመኖሪያ ቤቶች እጥረት ከፍተኛ በሆነባት ናይሮቢ የቁጥጥር ደንቦችን እየጣሱ በአቋራጭ የሚሰሩ የግንባታ ድርጅቶች በመብዛታቸው የህንጻዎች መደርመስ በጣም የተለመደ መሆኑ ተመልክቷል።

XS
SM
MD
LG