በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ልዮ መርምሪ ሮበርት ሞለር የመጀመሪያ መግለጫ


ልዮ መርምሪ ሮበርት ሞለር
ልዮ መርምሪ ሮበርት ሞለር

ልዮ መርምሪ ሮበርት ሞለር ሥራቸውን ካጠናቀቁ በኋላ ዛሬ በሰጡት የመጀመሪያ መግለጫ ከሀገሪቱ የፍርድ ሚኒስቴር በተሰጣቸው መመርያ መሰረት ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕን በወንጀል መክሰስ መሥርያ ቤታቸው ሊያስበው የማይችል ነገር ነበር ብለዋል።

የሮበርት ሞለር ልዩ መሥርያ ቤት ከሦስት ዓመታት በፊት በዩናይትድ ስቴትስ በተካሄደው የምርጫ ዘመቻ የሩስያ እጅ መግባትን አስመልክቶ ለ22 ወራት ያህል ምርመራ ሲካሄድ መቆየቱ የሚታወቅ ነው።

ሞለር የምርመራውን ሂደት ባለፈው መጋቢት ወር ሲያጠናቅቁ በዶናልድ ትረምፕ የምርጫ ዘመቻና በሞስኮ መካከል የመመሳጠር ተግባር መፈፀሙን የሚያረጋግጥ ማሰረጃ አልተገኘም ብለዋል።

ፕሬዚዳንት ትረምፕ የምርመራውን ሂደት ለማሰናክል ሞክረው እንደሆነ ግን የክስ ምክረ ሃስብ ለማቅረብ ባይችሉም እንኳን ነፃ ናቸው እንደማይሉ ባወጡት ባለ 448 ገፅ የምርመር ውጤት ግልፅ አድርገዋል።

ሞለር ለጋዜጠኞች ሲናገሩ “ፕሬዚዳንቱ ምንም ዓይነት ወንጀል አልፈፀሙም በሚለው ነጥብ ላይ ብንተማመን ኖሩ በግልፅ እናስቀምጠው ነበር” ብለዋል።

የዩናይትድ ስቴትስ ዋና ኣቃቤ ህግ ዊልያም ባር የሞለርን ዘገባ ከሌሎች ከፍተኛ የፍርድ ሚኒስቴር ባለሥልጣኖች ጋር ሆነን ከመረመርን በኋላ ትረምፕን የፍርዱን ሥርዓት ለማሰናክል በመሞከር ተግባር ለመክሰስ የምንችልበት በቂ ማስረጃ አልተገኝም ሲሉ ለሀገሪቱ ምክር ቤት አባላት ተናግረዋ ነበር።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG