በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የቀድሞው የዚምባብዌ ፕሬዚዳንት ሮበርት ሙጋቤ ረፍት


የቀድሞው የዚምባብዌ ፕሬዚዳንት ሮበርት ሙጋቤ
የቀድሞው የዚምባብዌ ፕሬዚዳንት ሮበርት ሙጋቤ

የቀድሞው የዚምባብዌ ፕሬዚዳንት ሮበርት ሙጋቤ አረፉ። ስለሙጋቤ ህልፈት በኦፊሴል ትዊተራቸው ያስታወቁት የወቅቱ ፕሬዚዳንት ኢመርሰን መናንጋግዋ ናቸው።

በ95 ዓመት እድሚያቸው ያረፉት ሙጋቤ ዚምባብዌ እአአ በ1980 ነጻነትዋን ከተጎናፀፈችበት ጊዜ አንስቶ ሀገሪቱን ለ37 ዓመታት ገዝተዋል። ሙጋቤ ከሁለት ዓመታት በፊት ከሥልጣን እንዲወገዱ ያደረገው የሀገሪቱ ወታደራዊ ኃይል ነው።

ሙጋቤ መጀመርያ ላይ በሀገሪቱ ነፃ አውጭነት ሲሞገሱ ነበር። ወደ ኋላ ግን የፖለቲካ ተቃዋሚዎችን መደብደብ፣ ሰቆቃ መፈፀምንና ግድያን ያካተቱ የሰብአዊ መብት ረገጣ ይፈፅማሉ በሚል ይነቀፉ ነበር።

የሙጋቤ ደጋፊዎች ከ19 ዓመታት በፊት የነጮች የእርሻ መሬቶችን መያዝ ሲጀምሩ የምዕራብ ሀገሮች ማዕቀቦች ጣሉባቸው።

እአአ በ2008የገንዘብ ግሽበት 231 ሚሊዮን ከመቶ ከደረሰ በኋላ ዚምባብዌ በራስዋ ገንዘብ መጠቀሙን አቆመች። በሳቸው ላይ ይሰነዘር የነበረው ነቀፊታም እየከረረ ሄደ።

የአፍሪካ ብሄራዊ ኮንግረስ ባወጣው የሀዘን መግለጫ “መላ ህይወታቸውን፣ ሀገራቸውንና ህዝባቸውን ሲያገለሉ አልፈዋል” ይላል።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG