ሀዋሳ —
የአፍሪካ ኅብረት ልዩ መልዕክተኛ ኦሊሴጉን ኦባሳንጆና የዩናይትድ ስቴትስ የአፍሪካ ቀንድ ልዩ ልዑክ አምባሳደር ጄፍሪ ፌልትማን ቀደም ሲል የጀመሩትን እውነታ የማፈላለግ ሥራና የሰላም ጥረት ለመቀጠል አዲስ አበባ መመለሳቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ገልፀዋል።
አምባሳደር ጄፍሪ ፌልትማን ከምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ጋር መወያየታቸውንም አምባሳደር ዲና ተናግረዋል።
ዛሬ በሃዋሳ ዩኒቨርሲቲ በተከፈተው የዲፕሎማሲ ማዕከል ላይ የተገኙት አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ከአሜሪካ ድምፅ ጋር ባደረጉት አጭር ቃለ ምልልስ “ኦባሳንጆ የሰሜኑን ጦርነት በተመለከተ ከተለያዩ ወገኖች ጋር የሚያደርጉትን ንግግር ይቀጥላሉ” ብለዋል።