በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የድንበር የለሽ ሀኪሞች ቡድን አባላት በሱዳን ታስረው ተለቀቁ


ፎቶ ፋይል፦ ሱዳን ዋና ከተማ ካርቱም
ፎቶ ፋይል፦ ሱዳን ዋና ከተማ ካርቱም

የድንበር የለሽ የሀኪሞች ቡድን 9 አባላቱ ከትናንት በስቲያ ሰኞ ጥር 18 ምሽቱን በሱዳን ባለሥልጣናት ካርቱም ውስጥ ተይዘው ከታሰሩ በኋላ በማግስቱ መለቀቃቸውን ዛሬ ባወጣው መግለጫ አስታወቀ፡፡

የቡድኑ አባላት የታሰሩት ከሚሰሩበት ሆስፒታል ወደ ቤታቸው ሲመለሱ መሆኑም ገልጾ ሌሊቱን በፖሊሶች ሰለሚሰሩት የህክምና ሥራ መጠየቃቸው ተመልክቷል፡፡

የሀኪሞቹ ቡድኑ የአስችኳይ ጉዳዮች ኃላፊ ሚሸል ኦሊቨር “የባልደረቦቻችን መታሰርና ስለህክምና ሥራዎቻቸው መመርመር ተቀባይነት የለውም” ብለዋል፡፡

ኃላፊዋ አክለውም ሀኪሞቹ መለቀቃቸው ተገቢ ቢሆንም ቀድሞውኑም ቢሆን ግን መታሰራቸው አግባብ አለመሆኑ ግልጽ ነው በማለት ተናግረዋል፡፡

ዓለምአቀፍ ድንበር የለሽ የሀኪሞች ቡድን በሱዳን ሁሉንም መስፈርት አሟልቶ ህጋዊ ፈቃድ ያለው መሆኑ በመግለጫው ጠቅሶ በሱዳን የሚገኘው፣ የህክምና እርዳታ ለሚያስፈልጋቸው ሰዎች እርዳታ ለመስጠት ብቻ መሆኑ አመልክቷል፡፡

የቡድኑ አባላት በእስር ቆይታቸው ምንም ዓይነት አካላዊ ጥቃት ያልደረሰባቸው መሆኑም ተገልጿል፡፡

XS
SM
MD
LG