በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በኤምኤስኤፍ ሠራተኞች ላይ ትግራይ ውስጥ የተፈፀመው ግድያ ብርቱ ውግዘት አስነሳ


The logo of Medecins Sans Frontieres (MSF - Doctors Without Borders)
The logo of Medecins Sans Frontieres (MSF - Doctors Without Borders)

ሦስት ሠራተኞቹ ትግራይ ውስጥ እንደተገደሉበት ድንበር የለሽ ሃኪሞች ቡድን (ኤም ኤስ ኤፍ) ትናንት አስታውቋል።

ሦስት ሠራተኞቹ ትግራይ ውስጥ እንደተገደሉበት ድንበር የለሽ ሃኪሞች ቡድን (ኤም ኤስ ኤፍ) ትናንት አስታውቋል።

የተገደሉት ሁለቱ ኢትዮጵያዊያን፣ አንዷ ስፓኛዊ ናቸው።

የኢትዮጵያና የዩናይትድ ስቴትስ መንግሥታት ግድያውን አውግዘዋል።

የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ በረድዔት ሠራተኞቹ ላይ ግድያው የተፈፀመው ህወሓት በሚንቀሳቀስበት አቢ አዲ አካባቢ መሆኑን ጠቁሞ “አድራጊዎቹም የህወሓት ታጣቂዎች ናቸው” ብሏል።

የህወሓት ቃል አቀባይ የሆኑት ጌታቸው ረዳ ዛሬ ባወጡት ትዊት “የእርዳታ ሠራተኞቹ ሾአተ ህጉም ውስጥ የተገደሉት በሚሸሹ የኢትዮጵያ ወታደሮች ነው” ብለዋል። አድራጎቱን “ብልሹና አሳዛኝ” ብለውታል።

የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ኔድ ፕራይስ ባወጡት መግለጫ በረድዔት ሠራተኞች ላይ የሚፈፀም ጥቃት ምንም አሳማኝ ምክንያት ሊቀርብበት የማይችል ጥፋት መሆኑን ገልፀው አጣዳፊ ምርመራ ተደርጎ የአድራጎቱ ፈፃሚዎች ለህግ እንዲቀርቡ አሳስበዋል።

የመንግሥታቱ ድርጅት ዋና ፀሃፊ አንቶኒዮ ጉቴሬሽ ዛሬ ባወጡት መልዕክት የኤም ኤስ ኤፍ ሠራተኞች መገደል በእጅጉ ያስደነገጣቸው መሆኑን አስታውቀዋል።

“ይህ ፈፅሞ ተቀባይነት የሌለውና አስፀያፊ የሆነ የዓለም አቀፍ ህግ ጥሰት ነው። የግድያው ፈፃሚዎች ተገኝተው በብርቱ መቀጣት አለባቸው። ትግራይ ውስጥ ለህዝቡ ከለላና ድጋፍ ለመስጠት ህይወታቸውን ለአደጋ እያጋለጡ የሰብዓዊ ተግባር አጋሮቻችን ጋር በድጋፍ እቆማለሁ” ብለዋል።

ዓለም አቀፍ የቀይ መስቀል ኮሚቴም በእርዳታ ሠራተኞቹ ላይ የተፈፀመውን ግድያ በብርቱ እንደሚያወግዝ አስታውቋል።

ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ

በኤምኤስኤፍ ሠራተኞች ላይ ትግራይ ውስጥ የተፈፀመው ግድያ ብርቱ ውግዘት አስነሳ
please wait

No media source currently available

0:00 0:02:45 0:00


XS
SM
MD
LG