በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በኮንጎ የኢቦላ ሥርጭት


ፎቶ ፋይል
ፎቶ ፋይል

ድንበር አልባ ሃኪሞች የተባለው የህክምና ግብረ ሰናይ ድርጅት በምሥራቅ ዲሞክራሲያዊ ኮንጎ ሪፖብሊክ በምትገኝ አንዲት ከተማ የሚያካሂደውን የኢቦላ በሽታ ሥርጭት መከላከል እንቅስቃሴ እና ሌሎችንም አገልግሎቶች ማቆሙን አስታወቀ።

ድንበር አልባ ሃኪሞች የተባለው የህክምና ግብረ ሰናይ ድርጅት ከዚህ ውሳኔ የደረሰው ቢያካቶ ከተማ ባሉት በርካታ የጤና ጣቢያዎች የታጠቁ የመንግሥት ወታደሮች በመስፈራቸው ምክንያት መሆኑን ገልጾ ከምንክተለው ከወገንተኝነት ነጻነት መርኃችን የሚጋጭ በመሆኑ ነው ብሏል።

የኤምኤስኤፍ የአጣዳፊ ሁኔታዎች ፕሮግራሞች ምክትል ሃላፊ ሲናገሩ ከጥቂት ሳምንታት በፊት ታጣቂዎች ባደረሱት ጥቃት ሦስት የፀረ ኢቦላ ሰራተኞች መገደላቸውንና ብዛት ያላቸው መቁሰላቸውን ገልጸው ያን ተከትሎ መንግሱ ወታደሮችን መላኩን ገልጸዋል

ጸጥታ ማስከበር አስፈላጊ መሆኑ እናምንበታለን ያሉት የድንበር የለሽ ሃኪሞች ባላሥልጣንዋ ሆኖም ሲቪሎች ወታደሮችን በመፍራት ወደጤና ጣቢያ ከመሄድ ይቆጠባሉ ሲሉ አስረድተዋል።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG