ዋሺንግተን ዲሲ —
ይሁን እንጂ የሞዛምቢክ የቀድሞው የገንዘብ ሚኒስትር ማኑኤል ቻንግ በደቡብ አፍሪካ እሥር ቤት ይቆያሉ።
ቻንግ በዩናይትድ ስቴትስ ክሥና ጥያቄ በደቡብ አፍሪካ አቋርጠው እየተጓዙ ሳሉ የተያዙት ባለፈው ታኅሣስ ነበር።
የቀድሞው የገንዘብ ሚኒስትር የተከሰሱት ከባሕር ልማት ፕሮጀክቶች ጋር በተያያዙ የሁለት ቢሊዮን ዶላር ምሥጢራዊ ግዥ ብድር ጉዳይ ሲሆን ይገዛሉ የተባሉት ግብአቶችና አገልግሎቶች ጨርሶ እንዳልታዩ ተገልጿል።
ሌሎች አራት ባለሥልጣናትም በጉቦ፣ በማጭበርበርና በወንጀል አድራጎት የተገኘን ገንዘብ ለማፅዳት በመሞከር ተከስሰዋል።
በብድር እንዲወጣ ከተወሰነው ገንዘብ ውስጥ 200 ሚሊየን የሚሆነው በራሣቸውና በሌሎችም የመንግሥቱ ባለሥልጣናት ሂሣቦች ገቢ እንዲደረጉ ከሃገር ውጭ ወደሚገኙ ባንኮች እንዲተላለፉ ትዕዛዞች መተላለፋቸውንም በኒው ዮርክ ምሥራቃዊ ወረዳ ፍርድ ቤት የተመሠረባቸው ክሥ ይናገራል።
የእነ ቻንግ ጉዳይ የፖለቲካ ገፅታ እየያዘ በመምጣቱ የጆሃንስበርጉ ችሎት ዶሴውን ምናልባት ወደ ደቡብ አፍሪካ የገንዘብ ሚኒስትር ሊመራው እንደሚችል እየተሰማ ነው።
የፌስቡክ አስተያየት መስጫ