በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በሞዛምቢክ የተቃዋሚው መሪ የምርጫውን ውጤት ባለመቀበል ተቃውሞ እንዲደረግ ጥሪ አቀረቡ

በሞዛምቢክ ባለፈው ጥቅምት በተካሄደው አጨቃጫቂ ምርጫ ገዢው ፓርቲ ማሸነፉን ሕገ መንግሥታዊው ምክር ቤት ትላንት መወሰኑን ተከትሎ የተነሳውን ሁከት ለመቆጣጠር በዋና ከተማው ጎዳናዎች ላይ ፖሊሶች ጥበቃ እያደረጉ ማፑቶ፣ ሞዛምቢክ፣ እአአ ኅዳር 8/2024
በሞዛምቢክ ባለፈው ጥቅምት በተካሄደው አጨቃጫቂ ምርጫ ገዢው ፓርቲ ማሸነፉን ሕገ መንግሥታዊው ምክር ቤት ትላንት መወሰኑን ተከትሎ የተነሳውን ሁከት ለመቆጣጠር በዋና ከተማው ጎዳናዎች ላይ ፖሊሶች ጥበቃ እያደረጉ ማፑቶ፣ ሞዛምቢክ፣ እአአ ኅዳር 8/2024

በሞዛምቢክ ባለፈው ጥቅምት በተካሄደው አጨቃጫቂ ምርጫ ገዢው ፓርቲ ማሸነፉን ሕገ መንግሥታዊው ምክር ቤት ትላንት መወሰኑን ተከትሎ፣ የተቃዋሚው መሪ ቬናሲዮ ሞንድላኔ ተቃውሞ እንዲደረግ ዛሬ ጥሪ አሰምተዋል።

የፖዴሞስን ፓርቲ ወክለው ለፕሬዝደንትነት የተወዳደሩት የተቃዋሚው መሪ ቬናሲዮ ሞንድላኔ በቀጥታ በፌስቡክ ባስተላለፉት መልዕክት የፍሬሊሞ ፓርቲውን ዳንኤል ቻፖን ፕሬዝደንትነት ያፀናውን የምክር ቤቱን ውሳኔ ነቅፈዋል።

“ፍትሃዊ ያልሆነውን ውሳኔ በሰላማዊ መንገድ መቃወማችንን መቀጠል አለብን” ያሉት ቬናሲዮ ሞንድላኔ “የሕዝቡ ድምጽ መደመጥ አለበት” ሲሉ አክለዋል።

ምርጫውን ተከትሎ በተነሳው ሁከት ከፖሊስ ጋራ በተከሰተ ግጭት ቢያንስ 130 ሰዎች መገደላቸውን አንድ የሲቪል ማኅበረሰብ ቡድን አስታውቋል።

ተቃዋሚዎችና የምርጫ ታዛቢዎች ገዢው ፍሬሊሞ ፓርቲ ድምጽ ሰርቋል የሚል ክስ ያሰማሉ። ፓርቲው ክሱን ያስተባብላል።

የምርጫ ኮሚሽኑ ምርጫው ተጭበርብሯል በሚለው ውንጀላ ላይ አስተያየት ሲሰጥ አይሰማም።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG