በሞዛምቢክ በተካሄደው አጨቃጫቂና የሰው ሕይወት በጠፋበት ምርጫ አሸናፊ የሆኑት ዳንኤል ቻፖ ዛሬ ቃለ መሃላ ፈጽመዋል። ሃገሪቱን አንድ ለማድረግ እንደሚሰሩ ቻፖ ተናግረዋል።
ቃለ መሃላው በከፍተኛ ጥበቃ ሥር ቢካሄድም ዛሬ በተደረገው ተቃውሞ ተጨማሪ ሰባት ሰዎች ሕይወታቸውን እንዳጡ ተዘግቧል።
ባለፈው ጥር ወር በተካሄደው ምርጫ አሸናፊ እንደሆኑ የታወጀው የ48 ዓመቱ የገዢው ፓርቲ ዳን ኤል ቻፖ፣ በጋዝ ሃብቷ የምትታወቀውን ሃገር ከ50 ዓመታት በላይ የገዛውን የፓርቲያቸውን የበላይነት አስቀጥለዋል።
ዛሬ በመዲናዋ ማፑቶ እና ናምፑላ በተሰነች ከተማ በተካሄደው ተቃውሞ ሰባት ሰዎች መገደላቸውን አንድ መንግሥታዊ ያልሆነ ተቋም አስታውቋል።
የተቃዋሚው ቬናንሲዮ ሞንድላኔ ደጋፊዎች ለወራት ተቃውሞ ሲያደርጉ ቆይተዋል። በየቀኑ በሚደረግ ተቃውሞ መንግሥትን እንደሚያሽመደምዱ ሞንድላኔ ዝተዋል።
የፍሪሊሞ ፓርቲ ምርጫውን ሰርቋል ሲሉ ሞንድላኔ ይከሳሉ።
ዓለም አቀፍ ታዛቢዎች ምርጫው ብዙ ጉድለቶች የታዩበት እንደሆነ አስታውቀዋል። የአውሮፓ ኅብረት በበኩሉ የምርጫው ውጤት መቀዩርን አመልክቶ ድርጊቱን አውግዟል።
መድረክ / ፎረም