በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በሞዛምቢክ የጀልባ አደጋ 96 ሰዎች ሞቱ


ሞዛምቢክ ሰሜናዊ የባህር ዳርቻ
ሞዛምቢክ ሰሜናዊ የባህር ዳርቻ

እንደነገሩ በተሠራ ጀልባ ላይ ሆነው ሲጓዙ የነበሩ 96 ሰዎች መሞታቸውንና 20 የሚሆኑት ደግሞ የደረሱበት እንደማይታወቅ የሞዛምቢክ ባለሥልጣናት አስታውቀዋል።

ጀልባዋ የሰመጠችው በሃገሪቱ ሰሜናዊ የባሕር ዳርቻ ትናንት እሁድ እንደነበር ታውቋል።

ጀልባዋ ቀድሞ ለዓሣ ማስገሪያነት የተሠራችና በኋላ ወደ መጓጓዣነት እንደተቀየረች እንዲሁም ከአቅሟ በላይ ተጭና እንደነበረ የአካባቢው ባለሥልጣናት አስታውቀዋል።

አንዳንዶቹ ተጓዦች በዩኔስኮ ቅርስነት በተመዝገበችው ሞዛምቢክ ደሴት ላይ ለሚደረግ ትርዒት በመጓዝ ላይ የነበሩ ሲሆን፣ ሌሎቹ ደግሞ በሃገሪቱ የተከሰተውን የኮሌራ ወረርሽኝ ሽሽት ላይ እንደነበሩ ተግሯል።

በዓለም ካሉ እጅግ ደሃ ሃገራት አንዷ በሆነችው ሞዛምቢክ፣ 15ሺሕ ሰዎች በኮሌራ እንደተያዙ ሲታወቅ፣ ካለፈው ጥቅምት ወዲህ 32 ሰዎች በበሽታው ሕይወታቸውን አጥተዋል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG