በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ከአንድ ወር በፊት ዩናይትድ ስቴትስ ድንበር ላይ የተለያዩ እናት እና ልጅ ተገናኙ


ከአንድ ወር በፊት ዩናይትድ ስቴትስ ድንበር ላይ የተለያዩ ጉዋቴማላዊት እናት እና የሰባት ዓመት ወንድ ልጃቸው ዛሬ ጠዋት ተገናኙ፡፡

ከአንድ ወር በፊት ዩናይትድ ስቴትስ ድንበር ላይ የተለያዩ ጉዋቴማላዊት እናት እና የሰባት ዓመት ወንድ ልጃቸው ዛሬ ጠዋት ተገናኙ፡፡

እናትና ልጅ ቦልቲሞር ዋሽንግተን አውሮፕላን ጣቢያ ላይ ነው የተገናኙት። ሊገንኙ የቻሉት እናቲቱ የዩናይትድ ስቴትስ ፍርድ ሚኒስቴርን በፌዴራል ፍርድ ቤት ከከሰሱ በሁዋላ ሚኒስቴሩ በቁጥጥር ሥር የነበረውን ልጅ ሊለቅ ከተስማማ በኋላ መሆኑ ታውቋል።

እናትየዋ ልጃቸውን ይዘው ድንበር ካቋረጡ በኋላ የፖለቲካ ጥገኝነት እንዲሰጣቸው ማመልከቻ አስገብተው ነበር። ማመልከቻቸው መልስ እሰከሚያገኝ ወደቴክሳስ ሄደው እዚያ እየኖሩ ይጠብቃሉ ።

ትናንት የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዶንት ዶናልድ ትረምፕ በሜክሲኮ ድንበር ገብተው የተነጣጠሉ ቤተሰቦችን እንዲያገናኙ ፌዴራል መንግሥት መሥሪያ ቤቶችን አሳስበዋል።

ትናንት የፕሬዚደንቱ ባለቤት መላኒያ ትረምፕ ቴክሳስ ውስጥ ከወላጆቻቸው የተነጠሉ የፍልሰተኛ ልጆች የተቀመጡበትን ማዕከል ጎብኝተዋል።

ቀዳማዊት እመቤቲቱ አስቀድሞ ይፋ ሳይደረግ በድንገት ያደረጉትን ጉብኝት፣ የለበሱት አወዛጋቢ ልብስ አጥልቶበታል።

ትናንት ሚላንያ ወደቴክሳስ ለመጓዝ ከሜሪላንድ ሲነሱ ጀርባው ላይ ‘I really don’t care , do you? እኔ ጉዳየ አይደለም እርሶስ? የሚል ፁሁፍ በትልልቁ የተፃፈበት ጃኬት ለብሰው ታየተዋል። የእርሳቸው ፅሕፈት ቤት ፁሁፉ የተደበቀ መልዕክት ለማስተላለፍ የታለመ እንዳልሆነ አጥብቆ እየተከራከረ ነው።

ፕሬዚዳንት ትረምፕ ግን ከዚያ የሚጋጭ ነገር በትዊት ፅፈዋል። የሜላኒያ መልዕክት በውሸት ዜና አሰራጭ ፌክ ኒውስ ሚዲያ ላይ ያነጣጠረ ነው። “ቀጣፊዎች መሆናቸው ገብቱዋታል ስለዚህ ግድ የላትም” ሲሉ አስነብበዋል።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG