በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ዩናይትድ ስቴትስ የጸረ-ሰው ፈንጂዎችን ጥቅም ላይ መዋል የሚያግድ አዲስ ፖሊሲ ይፋ አደረገች


ፎቶ ፋይል፦ በሴኦል የሚሳኤል ሙከራ የሚያሳይ ምስል ሰዎች በመከታተል ላይ
ፎቶ ፋይል፦ በሴኦል የሚሳኤል ሙከራ የሚያሳይ ምስል ሰዎች በመከታተል ላይ

የፕሬዚዳንት ጆ ባይደን አስተዳደር በዛሬው ዕለት እንዳስታወቀው አዲሱ ፖሊሲ የዩናይትድ ስቴትስን ጦር ሰራዊት የፀረ-ሰው ፈንጂዎችን ከመጠቀም ያግዳል። ይህም የዩናይትድ ስቴትስን ፖሊሲ ገዳይ እና ለጉዳት የሚዳርጉ ፈንጂዎችን ጥቅም ላይ እንዳይውሉ ከሚከለክለው ዓለም አቀፍ ሥምምነት ጋር የተጣጣመ ያደርገዋል።

ማስታወቂያው በቀድሞው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ ተሰጥቶ የነበረውን ፈቃጅ አቋም የቀለበሰ ሲሆን፤ ከአንድ ዓመት በላይ በዚያ አቋም ላይ ለተካሄደው ግምገማም ማብቂያ ይሆናል።

ፀረ-ሰው ፈንጂዎች ከምድር በታች ከተቀበሩበት፤ አለያም ተበታትነው ከወዳደቁበት በመፈንዳት ጥቅም ላይ የዋሉበት ጦርነቱ ካበቃ ረዥም ጊዜም በኋላ በሰላማዊ ሰዎች ላይ ሞትን ጨምሮ ብርቱ አደጋ ሊያስከትሉ ይችላሉ።

በአዲሱ ፖሊሲ ዩናይትድ ስቴትስ ደቡብ ኮሪያን ከሰሜን ኮሪያ ወረራ ለመከላከል ከምታደርገው ጥረት ውጪ እነዚህ ፈንጂዎች ጥቅም ላይ እንዳይውሉ ትገድባለች።

XS
SM
MD
LG