በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

አዲስ ሪፖርት፡ በዓለም ዙሪያ የታሰሩ ጋዜጠኞች ብዛት


ሲፒጄ
ሲፒጄ

በዓለም ዙሪያ የታሰሩ ጋዜጠኞች ብዛት ከፍተኛ መሆኑን፣ ሲፒጄ አስታወቀ።

ለጋዜጠኞች መብት የቆመው ኮሚቴ/ሲፒጄ/ ዛሬ ባወጣው፣ ዓመታዊ ጥናት ዘገባ ነው ይሄን ያመለከተው።በዓለም ደረጃ ጋዜጠኞችን በብዛት የሚያስሩት ቻይና፣ ቱርክ፣ ሳውዲ አረብያና ግብጽ መሆናቸውን፣ ዘገባው ጠቁሟል።

በዓለም ደራጃ ለአራት ተከታታይ ዓመታት፣ በመቶዎች የሚቆጠሩ ጋዜጠኞች መታሰራቸው የቀጠለ መሆኑን፣ ሲፔጄ ያወጣው ዘገባ ጠቁሟል።

ሺ ዢንፒንግን፣ ረጂፕ ታይፕ ኤርድዶዋንን፣ ሞሐመድ ቢን ሳልማንንና ዐብደል ፍታሕ ዐል-ሲሲን የመሳሰሉት አምባገነን መሪዎች፣ የሚነቅፍ ሚድያን ማሳደደን ቀጥለዋል ይላል ዛሬ የወጣው ዘገባ።

በዓለም ደረጃ በእስር የሚገኙት ጋዜጠኞች ብዛት፣ በያዝነው ዓመት ከ253 ወደ 245 ዝቅ ማለቱን፣ ዘገባው ጠቅሷል።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG