በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

አንድ የሞስኮ ችሎት እስር ላይ የሚገኘውን አሜሪካዊ ጋዜጠኛ ይግባኝ አልሰማም አለ


የዎል ስትሪት ጆርናል ጋዜጣ ዘጋቢ ኢቫን ጌርሽኮቪች
የዎል ስትሪት ጆርናል ጋዜጣ ዘጋቢ ኢቫን ጌርሽኮቪች

የሞስኮው ፍርድ ቤት በዛሬው ዕለት የዎል ስትሪት ጆርናል ጋዜጣ ዘጋቢ ኢቫን ጌርሽኮቪች ከፍርድ ሂደቱ አስቀድሞ ለሦስት ወራት የተራዘመውን እስር በመቃወም ያቀረበውን ይግባኝ አልሰማም አለ።

የዛሬው የችሎቱ ውሳኔ፤ ባለፈው የግንቦት ወር ለመጀመሪያ ጊዜ የተደረገውን ጨምሮ በከሰሰበት ወንጀል ከመፈረዱ አስቀድሞ እስሩ ሁለት ጊዜ ለተራዘመው ጌርሽኮቪች ራሱን ለመከላከል በያዘው ጥረት የቅርብ ጊዜው ፈተና ነው።

የቅድመ ፍርድ እስራቱ በግንቦት ወር መገባደጂያ ያበቃል ቢባልም፤ መጀመሪያ እስከያዝነው የነሐሴ ወር ከዚያም ዳግም እስከ መጭው የሕዳር ወር ድረስ ተራዝሟል።

“ፍርድ የሚሰጥበት ቀንም አልተወሰነም”

በሥለላ ድርጊት ተወንጅሎ ካለፈው የመጋቢት ወር አንስቶ እስር ላይ የሚገኘው ጌርሽኮቪች፡ የሚሰራበት ጋዜጣ ዎል ስትሪት ጆርናል’ም ሆነ የዩናይትድ ስቴትስ መንግሥት ‘በግፍ ነው’ የታሰረው ሲሉ፤ የቀረበበትን ውንጀላ አጥብቀው ያስተባብላሉ።

“ፍርድ የሚሰጥበት ቀንም አልተወሰነም” ሲል የድንበር የለሹ የሃኪሞች ማሕበር የዩናይትድ ስቴትስ ቅርንጫፍ አስታውቋል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG