በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ሞሮኮ 25 አፍሪካዊ ፍልሰተኞችን ይዣለሁ አለች


ፎቶ ፋይል፦ የሞሮኮ ፖሊስ
ፎቶ ፋይል፦ የሞሮኮ ፖሊስ

የሞሮኮ ፖሊስ ሃገሪቱን ከስፔን ጋር ከሚያዋስነው እና ባለፈው የሰኔ ወር ድንበር አቋርጠው ለማለፍ ሲሞክሩ 23 ሰዎች ከሞቱበት ስፍራ ያገኛቸውን ሃያ-አምስት አፍሪካውያን ፍልሰተኞች መያዙን በትናንትናው ዕለት አስታወቀ።

የሞሮኮ ፍርድ ቤቶች ሱዳናውያን የሚበዙባቸው በርካታ ስደተኞች ወደ ዚያች አገር በሕገ-ወጥ መንገድ በመግባት እንዲሁም በፀጥታ ሠራተኞች ላይ ሁከት በመፍጠር ጥፋተኛ በሚል ከፍተኛ የእስር ቅጣት ከበየኑ በኋላ ትናንት የተያዙት ስደተኞች ዜና የመጀመሪያው ነው ነው።

አንድ የፍርድ ቤት ምንጭ ለኤ.ኤፍ.ፒ የዜና ወኪል እንደተናገሩት፣ መሊላ-ስፔን አቅራቢያ ከአውሮፓ ህብረት ጋር ድንበር በሚጋራውና ለየት ባለው የአፍሪካ ድንበር ውስጥ በሚገኝ ጉሩጉ ጫካ ውስጥ ከቻድና ከሱዳን የመጡ ቁጥራቸው 25 የሚደርሱ ፍልሰተኞች በቁጥጥር ሥር ውለዋል።

ባለሥልጣናቱን ፍልሰተኞቹን በሚይዙበት ወቅት “ሁከት ፈጥረዋል” በሚል እንደሚወነጅሏቸው ተዘግቧል። ትላንት የተያዙትም በመጪው ሰኞ አቃቤ ህግ ፊት እንደሚቀርቡ ተገልጧል።

“ሞሮኮ ለአውሮፓ የፍልሰተኞች ህግ እንደ ፖሊስ እያገለገለች ነው” ሲሉ ኦማር ናጂ የተባሉ የሰብዓዊ መብት ድርጅት ሃላፊ ራባትን ወንጅለዋል። “ባለሥልጣናት እነዚህን ፍልሰተኞች መያዝ ሳይሆን መንከባብ ነው የነበረባቸው” ሲሉም ናጂ አክለዋል።

ጉሩጉ ጫካ አፍሪካውያን ፍልሰተኞች ከፍተኛ ጥበቃ የሚደረግለትን የመሊላ ድንበር ጥሰው አውሮፓ ከመግባታቸው በፊት ጊዜያዊ ድንኳን ተክለው የሚቆዩባት ሥፍራ ነች።

ባለፈው ሰኔ በአብዛኛው ሱዳናውያን የሆኑ 2000 ፍልሰተኞች በኃይል ጥሰው ለመግባት ሞክረው ነበር። በዚህ ሙከራ ቢያንስ 23 ፍልሰተኞች ለህልፈት ተዳርገዋል። ይህም ለዓመታት ያልታየ የከፋ አደጋ ነው በሚል የሰብዓዊ መብት ድርጅቶች የሞሮኮንና የስፔንን የጸጥታ ኃይሎች ከልክ በላይ ኃይል በመጠቀም ይወነጅሏቸዋል።

XS
SM
MD
LG