በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የሴኔጋል ባሕር ኃይል 338 ፍልሰተኞችን ያዘ

የሴኔጋል ባሕር ኃይል፣ 338 ፍልሰተኞችን ከባሕር ዳርቻው 150 ኪሜ ርቀት ላይ መያዙን አስታውቋል።
የሴኔጋል ባሕር ኃይል፣ 338 ፍልሰተኞችን ከባሕር ዳርቻው 150 ኪሜ ርቀት ላይ መያዙን አስታውቋል።

የሴኔጋል ባሕር ኃይል፣ 338 ፍልሰተኞችን ከባሕር ዳርቻው 150 ኪሜ ርቀት ላይ መያዙን አስታውቋል።

35 ሴቶች እና 13 ታዳጊዎች እንደሚገኙበት ካፒቴን አማዱ ዲያሎ የተባሉ የባሕር ኃይሉ አባል ለኤኤፍፒ ዜና ወኪል አስታውቀዋል።

ባለፉት ሁለት ቀናትም በተመሳሳይ ፍልሰተኞችን ከባሕር ላይ መያዛቸውን ካፕቴኑ ገልጸዋል።

ባሕር ኃይሉ ፍልሰተኞችን ይዞ ወደ መጡበት በመመለስ ረገድ ከሌሎች የመንግስት ቢሮዎች ጋር በመሆን ሚና እየተጫወተ መሆኑን ያወሱት ካፕቴ አማዱ፣ ወደ አውሮፓ ለመሻገር የሚሞክሩትን ፍልሰተኞች ለመያዝ አሠራር መቀመጡን ጠቁመዋል።

የስፔኗ ካናሪ ደሴት ከምዕራብ አፍሪካ ለሚነሱ ፍልሰተኞች መዳረሻ መሆኗ ሲታወቅ፣ ከሁለት ሳምንታት በፊት፣ በአንድ ቀን ብቻ፣ 900 የሚሆኑ ፍልሰተኞች ደሴቲቱ ደርሰዋል።

ሕገ ወጥ አዘዋዋሪዎች በአሁኑ ወቅት ያለውን መልካም የአየር ጸባይ ስለሚጠቀሙ፣ የፍልሰተኞቹ ቁጥር ሊጨምር መቻሉ ታውቋል።

በሜዲትሬንያን ባሕር በኩል ያለው ቁጥጥር ጠበቅ በማለቱም፣ በሰላማዊ ውቂያኖስ በኩል ወደ አውሮፓ ለመሻገር የሚሹ ፍልስተኞች ቁጥር ሊጭምር መቻሉም ተመልክቷል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG