በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ከኢትዮጵያና ከኤርትራ አዋሳኝ አካባቢዎች የተወከሉ ነዋሪዎች

ከኢትዮጵያና ከኤርትራ አዋሳኝ አከባቢዎች የተውጣጡ ነዋሪዎች ዛሬን አብረው ለመዋል ቀደም ሲል ይዘውት በነበረ ዕቅድ መሠረት በሺሆች እንደሚቆጠር የተነገረ የራማና የአካባቢው ሰው መረብ ወንዝ ዳር ሲገኝ ከኤርትራዪቱ ክሳድ ዒቃ ኤርትራ ግን አለመገኘታቸው ታውቋል።

ከኢትዮጵያና ከኤርትራ አዋሳኝ አከባቢዎች የተውጣጡ ነዋሪዎች ዛሬን አብረው ለመዋል ቀደም ሲል ይዘውት በነበረ ዕቅድ መሠረት በሺሆች እንደሚቆጠር የተነገረ የራማና የአካባቢው ሰው መረብ ወንዝ ዳር ሲገኝ ከኤርትራዪቱ ክሳድ ዒቃ ኤርትራ ግን አለመገኘታቸው ታውቋል።

ከኤርትራ ወገን ያልተገኙት ፍቃድ ስላልተሰጠ መሆኑን የኤርትራ ሠራዊት አባላት እንደነገሯቸው ቪኦኤ ያነጋገራቸው የራማ ነዋሪዎች ገልፀዋል።

ዘግየት ብለው መጡ የተባሉ መልእክተኞች እንዳሉት ደግሞ የክሳድ ዒቃ ሰዎች ያልተገኙት በመረጃ ልውውጥ ችግር ሲሆን መጭውን ቅዱስ ዮሃንስን አብረው ለመዋል ቀጠሮ መያዛቸው ተነግሯል።

በሌላ በኩል ደግሞ ከ50 በላይ የሰቲት ሑመራ ነዋሪዎች ዛሬ ተከዜ ወንዝን ተሻግረው ከኤርትራውያንና ከኤርትራ ሠራዊት ጋር ተወያይተው መመለሳቸው ታውቋል። ወደ ኡምሐጀር ከተማ ለመግባት ግን እንዳልተሳካም ገልፀዋል።

ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ

ከኢትዮጵያና ከኤርትራ አዋሳኝ አካባቢዎች የተወከሉ ነዋሪዎች
please wait

No media source currently available

0:00 0:05:28 0:00

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG