በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ዚምባቡዌ:- ኩፍኝ ከመቶ ሃምሳ በላይ ህፃናት ገደለ


ፎቶ ፋይል - እናቶች ልጆቻቸውን የክፉኝ በሽታ ለማስከተብ እየተጠባበቁ፣ ሃራሬ ከተማ ማብቩኩ ዚምባብዌ እአአ 8/2022
ፎቶ ፋይል - እናቶች ልጆቻቸውን የክፉኝ በሽታ ለማስከተብ እየተጠባበቁ፣ ሃራሬ ከተማ ማብቩኩ ዚምባብዌ እአአ 8/2022

ዚምባቡዌ ውስጥ የተቀሰቀሰው የኩፍኝ ወረርሽኝ አንድ መቶ ሃምሳ ሰባት ህፃናት መግደሉን የሃገሪቱ መንግሥት አስታወቀ።

በመላ ሃገሪቱ ከሁለት ሺህ በላይ ሰው መያዙንም ባለሥልጣናቱ አክለው ገልፀዋል።

የመጀመሪያው የኩፍኝ ተጋላጭ መገኘቱን የጤና ባለሥልጣናቱ ያስታወቁት ከጥቂት ቀናት በፊት ሲሆን ለህልፈት የተዳረጉት ህፃናት ቁጥር ከአንድ ሳምንት ባነሰ ጊዜ ውስጥ በእጥፍ ገደማ መጨመሩን አመልክቷል።

ለወረርሽኙ ከተጋለጡት አብዛኞቹ የመከላከያውን ክትባት ያልወሰዱ መሆናቸውን የማስታወቂያ ሚኒስትሯ ሞኒካ ሙትስቫንጓ ተናግረዋል።

የየማኅበረሰብና የሃይማኖታዊ መሪዎች ህዝቡ እንዲከተብ በመቀስቀስ እንዲያግዙ መንግሥቱ መጠየቁን ሚኒስትሯ አክለው አመልክተዋል።

XS
SM
MD
LG