አዲስ አበባ —
ኢትዮጵያ ውስጥ እያደገ የመጣው የሰብዓዊ ዕርዳታ ፍላጎት ከሚሰጠው ምላሽ ጋር ሊጣጣም እንዳልቻለ በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሰብዓዊ ጉዳዮች ማስተባበሪያ - ኦቻ የአዲስ አበባ ፅሕፈት ቤት አስታውቋል፡፡
ግብረ ሰናይ ድርጅቶች ከለጋሾች ጋር በመተባበር ተጨማሪ ገንዘብ ለማግኘት እየጣሩ መሆናቸውን ቢሮው ገልጿል፡፡
ኤል ኒኞ በያዝነው ዓመት ውስጥ ሊያስከትል የሚችለውን ጉዳት ለመቋቋም ዕቅድ እየተዘጋጀ መሆኑንም የሰብዓዊ ጉዳዮች ማስተባበሪያ ፅሕፈት ቤቱ አመልክቷል፡፡
ለተጨማሪ የተያያዘውን ዘገባ ያዳምጡ፡፡