በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ አዳዲስ የኩፍኝ ወረርሽኝ ተገኘ


ዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ፣ እአአ ከ1992 ወዲህ ታይቶ የማይታወቅ በከፍተኛ ደረጃ የተሰራጨ 33 አዳዲስ የኩፍኝ ወረርሽኝ ባለፈው ሳምንት ብቻ መገኘቱ ተገለፀ።

የአዲሱን ስርጭት ጠቅላላ ድምር 107 እንዳደረሰው፣ የጤና አገልግሎት ባለሥልጣኖች አመልክተዋል።

አስከፊ የተባለው ከፍተኛ ስርጭት፣ ከሃያ-አምስት ዓመት በፊት የነበረውና 2,126 ህሙማን የተመዘገቡበት መሆኑ ይታወሳል።

ወረርሽኙ በ33 ሴቴቶች መዛመቱ የተገለፀ ሲሆን በተለይ በካሊፎርኒያ፣ በኒው-ዮርክ፣ በፔንሲልቬንያና በዋቪንግተን ስቴት ስርጭቱ እንደቀጠለ ተገልጧል።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG