ዋሽንግተን ዲሲ —
የሰሜን አትላንቲክ ቃል ኪዳን ሀገሮች ድርጅት ወይም ኔቶ (NATO) ትንሽዋን የኤድሪያቲክ ሃገር ሞንትኔግሮን አባሉ እንድትሆን በኦፊሴል ጋብዟል። ከስድስት አመታት ወዲህ የአባላቱን ቁጥር ሲያሰፋ ለመጀመርያ ጊዜ ነው።
የኔቶ (NATO) ዋና ጸሃፊ ጀንስ ስቶልተንበርግ(Jens Stoltenberg) ዛሬ ስለጉዳዩ ያስታወቁት በ ኔቶ (NATO) የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ስብሰባ ላይ ነው። የይጎዝላቭያ አካል ለነበረችው ሃገር “ታሪካዊ ስኬት ነው” ብለውታል።
ሞንትኔግሮ NATO በሚጠይቀው መሰረት ብዙ ለውጦች ያደረገች ቢሆንም በኦፌሴል አባል ለመሆን ገና ማሟላት ያለባት ነገሮች አሉ።
የሞንትኔግሮ ካርታ
የሞንትኔግሮ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ኢጎር ሉክሲክ (Igor Luksic) ዛሬ ብራሰልስ በተደረገው ስብሰብ ቀርበው ሲናገሩ ግንዣውን “ትልቅ ክብርና ታሪካዊ” ብለውታል። ሞንትኔግሮ ነጻ ሀገር የሆነችው ከ 9 አመታት በፊት መሆኑ ይታወቃል።