በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ራሱን በራሱ ፎቶ ግራፍ ያነሳው ዝንጀሮ "ሰልፊ" የፈጠራ ባለቤትነት ገንዘብ ሊጋራ ነው


ከሰባት ዓመታት በፊት እንዲህ ሆነ …..እንግሊዛዊው ፎቶ አንሺ ዴቪድ ስሌተር ኢንዶኔዥያ ውስጥ ሲዘዋወር አንድ ቀን ካሜራውን እንደዋዛ ቁጭ አድርጎት ዞር ይላል።

ከሰባት ዓመታት በፊት እንዲህ ሆነ …..እንግሊዛዊው ፎቶ አንሺ ዴቪድ ስሌተር ኢንዶኔዥያ ውስጥ ሲዘዋወር አንድ ቀን ካሜራውን እንደዋዛ ቁጭ አድርጎት ዞር ይላል።

ምን ቢሆን ጥሩ ነው አጅሬ ባለጎፈሩ ዝንጀሮ ናሩቶ ካሜራውን ላፍ ያደርግና ሲነካካ ራሱን ሰልፊ ገጭ ማድረግ!

ናሩቶ ወጣ ወጣ ያሉትን ጥርሶቹን እያሳየ እነዚያን አምበር የመሳሰሉ ዓይኖቹን ካሜራው ሌንስ ላይ ተክሎ የሚታይበት ፎቶ የፎቶግራፍ አንሺው ኩባኒያ ዌብ ሳይት ላይ ከፍተኛ፣ እጅግ በጣም ተወዳጅነት አተረፈ።

ያ በሆነ በአራት ዓመቱ በ2015 ማለት ነው “ለእንስሳት ትክክለኛ አያያዝ የቆሙ ተሙዋጋቾች” የሚባል

ቡድን የዚያ ፎቶ ባለቤትነት መብት ያለው ሰልፊውን ያነሳው ዝንጀሮ አቶ ናሩቶ ነው ብሎ ፎቶግራፍ አንሺ ዴቪድ ስሌተርን ፍርድ ቤት አቆመው። በዚያ ሰልፊ የሚገኝ የገንዘብ ጥቅም ኃላፊነት ያለው ናሩቶ ነው ብሎ ቡድኑ ሙግት አነሳ።

የፎቶ አንሺው የስሌተር ወገን ደግሞ “የስሌተር ኩባኒያ ዋይድላይፍ ፐርሰናሊቲስ ከብሪታንያ ኮፒራይት ቢሮ የባለቤትነት መብት አግኝቷል፣ ሊከበርለት ይገባል” ብሎ ተከራከረ።

ከትናንት በስቲያ ሰኞ ታዲያ የዱር አራዊት መብት ተሙዋጋቹ ድርጅት /PETA/ እና ፎቶ አንሺው ከስምምነት ደረሱ። ስሌተር ከአሁን በኋላ ከናሩቶ ፎቶ ከሚያገኘው ገቢ ሃያ አምስት ከመቶውን ኢንዶኔዥያ ውስጥ ለሚገኙ ባለጎፈር ዝንጆሮዎች ደህንነት ለቆሙ በጎ አድራጎት ቡድኖች ሊያካፍል ተስማሙ።

“እንስሳት የፈጠራ ባለቤትነት መብት ሊኖራቸው አይችልም” ብሎ የበታች ፍርድ ቤት የሰጠውን ብይን የሳንፍራንሲስኮው ዘጠነኛው ይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤት እንዲሰርዘው የሁለቱም ወገኖች ጠበቆች ጠይቀዋል።

ለመሆኑ ናሩቶ እነዚያን ፍልጥ ጥርሶቹን ፍልቅልቅ አድርጎ ጉብ ብሎ ከሚታይበት ሰልፊ እስካሁን ፎቶ አንሺው ስሌተር ምን ያህል ገቢ አግኝቶበት ይሆን? ወደፊት ከሚያመጣው ገቢስ ሰባ አምስት ከመቶውን በጠቅላላ ኪሱ ያደርጋል? ጠበቆቹ ለመናገር ፈቃደኛ አልሆኑም። ዘጠነኛው ይግባኝ ሰሚ ችሎትም ገና ውሳኔ አልሰጠም

፡፡

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG