በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በኢራን የተቃውሞ እንቅስቃሴ ከተጀመረ ወዲህ 516 ሰዎች ተገድለዋል


የተቃዋሚ ሰልፈኞች
የተቃዋሚ ሰልፈኞች

በኢራን ጸረ መንግሥት ተቃውሞ ከአራት ወራት በፊት ከተቀሰቀሰ ወዲህ 516 ተቃዋሚ ሰልፈኞች መገደላቸውን መቀመጫው ዩናይትድ ስቴትስ የሆነ የሰብዓዊ መብት ተቆጣጣሪ ቡድን ተናገረ።

በእንግሊዝኛ የአህጽሮት መጠሪያው ሂራና የተባለው የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች የዜና አገልግሎት ትናንት ሰኞ ባወጣው መግለጫ ከተገደሉት መካከል ሰባ ልጆች እንደሚገኙባቸው አመልክቷል።

ከ19 ሺህ 200 የሚበልጡ ሰዎች መታሰራቸውን እና ከመካከላቸው 687ቱ ተማሪዎች መሆናቸውን አክሎ ገልጿል።

ባለፈው መስከረም ወር አጋማሽ የተቃውሞ ሰልፉ የተቀሰቀሰው ማህሳ አሚኒ የተባለች የ22 ዓመት ወጣት የአለባበስ ደንብ አላከበርሽም ተብላ በፖሊስ ቁጥጥር ስር ሳለች ህይወቷ ማለፉን ተከትሎ እንደነበር ይታወሳል።

XS
SM
MD
LG