የሞልዶቫ ፓርላማ ሩሲያ በያዝነው የክረምት ወር የአውሮፓ ኅብረት እጩ ወደሆነችው ሀገር ትልክ የነበረውን የተፈጥሮ ጋዝ አቅርቦት ልታቋርጥ ትችላለች በሚል ሥጋት በኃይል አቅርቦቱ ዘርፍ ተፈጻሚ የሚኾን የአስቸኳይ ጊዜ ዐዋጅ አጽድቋል።
101 መቀመጫዎች ያሉት የሞልዶቫ ምክር ቤት ከመጭው ሰኞ አንስቶ የሚጀምር እና ለ60 ቀናት የሚዘልቅ የአስቸኳይ ጊዜ ዐዋጅ ለማጽደቅ ድምጽ ሰጥቷል።
በዐዋጁም መሠረት ሞስኮ ለትልቁ የሞልዶቫ የጋዝ ማመንጫ ‘ኩሲዩርጋን’ የምታቀርበውን የጋዝ አቅርቦት የምታቋርጥ ከኾነ “አይቀሬ ፈተና” ይደቅናል ያሉትን ሁኔታ ይመራል። የኩሲዩርጋን የኃይል ማመንጫ በሩሲያ ዘመሙ የትራኒስትሪያ ግዛት ይገኛል።
እንደ አውሮፓውያን የዘመን አቆጣጠር በ2022 መገባደጃ ሩሲያ ከሞልዶቫ በምትዋሰነው ዩክሬን የከፈተችውን ጥቃት ተከትሎ የኩሲዩርጋን የኃይል ማመንጫ ሥራ ተቋርጦ ነበር።
መድረክ / ፎረም