በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በኤርትራ ሰዎች በየቤታቸው እንዲቆዩ የሚያስገድደው ዐዋጅ


አስመራ ከተማ
አስመራ ከተማ

በኤርትራ ሰዎች በየቤታቸው እንዲቆዩ የሚያስገድደው ዐዋጅ ባለበት እንሚቀጥል ተገለጸ። ባለፈው መጋቢት 24 የወጣውን ሰዎች ለ21 ቀናት በቤታቸው እንዲቆዩ የሚያስገድደው ዐዋጅ ተጨማሪ መመርያ እስኪሰጥ ባለባት ጸንቶ እንዲቀጥል የኤርትራ የኮሮናቫይረስ ወረርሽን ከፍተኛ ግብረኃይል አስታወቀ። የበሽታውን አደገኛነትን ግምት ውስጥ በማስገባት ከኤርትራ ነዋሪ ሁኔታ ጋር ወረርሽኙን ለመቆጣጠር ብቸኛው አማራጭ የሰውን እንቅስቃሴ መገደብ መሆኑ ስለታመነበት ዐዋጁ ባለበት ጸንቶ እንዲቀጥል እንደተወሰነ ከፍተኛ ግብረኃይሉ አስታውቋል።
በሌላ በኩል በኤርትራ በኮሮናቫይረስ ከተያዙ 39 ሰዎች መካከል ስድስቱ ከህመሙ በማገገማቸው ወደ ቤታቸው መሽኘታቸውን የኤርትራ ጤና ሚኒስተር አስታወቋል።

ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

በኤርትራ ሰዎች በየቤታቸው እንዲቆዩ የሚያስገድደው ዐዋጅ
please wait

No media source currently available

0:00 0:03:40 0:00


XS
SM
MD
LG