ሰሜን ኢትዮጵያ ውስጥ በተካሄደው ጦርነትና ግጭቶች ምክንያት የወደሙና የተጎዱ የጤና ተቋማትን መልሶ የመገንባት ሥራ በከፊል መጀመሩን የጤና ሚኒስቴር ዛሬ አስታውቋል።
በአማራ እና አፋር ክልሎች በጦርነቱ ምክንያት ከወደሙ ሆስፒታሎች ውስጥ 36ቱ ሥራ መጀመራቸው ተገልጿል። በግጭቶቹ ከ 3000 በላይ የጤና ተቋማት ጉዳት እንደደረሰባቸው የጤና ሚኒስትር ደ’ኤታ ዶ/ር አየለ ተሾመ ለጋዜጠኞች ተናግረዋል።
ዘገባው የፀሐይ ዳምጠው ነው።